ከ«ግብረ ስጋ ግንኙነት» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
መስመር፡ 107፦
 
==ፆታዊ የአካል ልዩነት==
[[Image:Male and female pheasant.jpg|thumb|upright=1.1|right|የአንዳንድ አእዋፍ አይነቶችዝርያዎች የፆታዊ አካል ልዩነት በመልክም በመጠንም አኳያ ይንፀባረቃል]]
 
ብዙ እንሥሣት በመልክም ሆነ በመጠን ልዩነት ያሳያሉ። ይህ ክስተት ፆታዊ የአካል ልዩነት (sexual dimorphism)በመባል ይታወቃል። ፆታዊ የአካል ልዩነት ከወሲባዊ ምርጠት (sexual selection)- ተመሣሣይ ፆታ ያላቸው ግላዊ ፍጡራን ከተቃራኒ ፆታ ጋር ለመዳራት የሚያደርጉት ፉክክር- ጋር የተቆራኘ ነው። የአጋዘን ቀንድ ላምሣሌ ወንዶቹ ከሴቶቹ ጋር የመዳራት እድል ለማግኘት ለሚያደርጉት ፍልሚያ ያሚያገለግል ነው። በአብዛኛው የአንድ ዝርያ የወንድ ፆታ አባሎች ከሴቶቹ በአካል ይገዝፋሉ። በአጥቢ እንሥሣት ውስጥ ክፍተኛ ፆታዊ የአካል ልዩነት ከታየ ከዚሁ ጋር ተያይዞ አንድ ወንድ ብቻውን ከብዙ ሴቶች ጋር የመዳራት ሁኔታ ይታያል። ይህም የሚሆነው በአካባቢው በሚገኙት ግላውያን ወንዶች መካከል በሚከስተው የጋለ የድሪያ መብት ማረጋገጫ ፍልሚያ ምክንያት ነው።
መስመር፡ 113፦
በሌሎች እንሥሣት፣ ነፍሳትንና አሦችን ጨምሮ፣ ሴቶቹ በአካል ከወዶቹ ይገዝፋሉ። ይህ ሁኔታ የድቀላ እንቁላልን ከማዘጋጀት ጋር የተያያዘ ነው ለማለት ይቻላል። ቀድም ሲል እንደተወሳው የእንስትን የዘር ቅንቁላል ወይንም ፍሬ ማዘጋጀት፣ የተባእትን የዘር ህዋስ ከማዘጋጅት ይልቅ ብዙ የንጥረነገር ቅምር ይጠይቃል። በአካል የገዘፉ እንስታን ብዙ የዘር እንቁላል መሥራት ይችላሉ። አንዳንድ ግዜ ይህ ፆታዊ የአካል ልዩነት እጅግ የበዛ ከመሆኑ የተነሳ ወንዶቹ የሴቶቹ ጥገኛ በመሆን ብቻ ተወስነው እንዲቀሩ ያደርጋል።
 
በአእዋፍ ውስጥ ወንዶቹ በአብዛኛው በህብረቀለም የተዋቡ (ለምሣሌ እንደ ተባእት የገነት ወፍ) ሆነው ይታያሉ። ይህ ሁኔታ አንዳንድ ፍጡራንን ለኑሮ በጂ ያልሁነ ሁኔታ ላይ ይጥላቸዋል የሚል አመለካከት አለ። (ለምሣሌ ህብራዊ ቀለም አንድን ወፍ ለአጥቂዎች በግልፅ እንዲታይ ያደርገዋል) ከዚህ በተፃፃሪነት ደግሞ የስንኩልነት መግለጫዘይቤ (handicap principle)የሚባል አመለካከት አለ። ይህ አመለካከት ወንዱ ወፍ ራሱን ለአጥቂዎች አጋልጦ በማሳየቱ፣ ነገዳዊ ጥንካሬውንና ድፍረቱን ለሴቶቹ ይገልፃል ይላል።
 
ሰብአዊ ፍጡራን፣ ወንዶቹ አጠቃላይ የሰውነት ግዝፈትና የሰውነት ፀጉር በመያዝ እንዲሁም ሴቶቹ ተለቅ ያሉ ጡቶችን በማውጣት፣ ስፋ ያሉ ዳሌዎችን በመያዝና ከፍ ያለ የውስጥ ሰውነት ቅባታዊ ይዘት በማፍለቅ የፆታ አካልዊ ልዩነትን ያሳያሉ።