ከ«ግብረ ስጋ ግንኙነት» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 1፦
'''ግብረ ስጋ ግንኙነት''' ወይም '''ሩካቤ ስጋ''' ማለት በሴትና በወንድ መካከል ለስሜት እርካታ የሚደረግ ግንኙነት ወይም ፍቅር መሥራት ነው። ይህም ለመባዛት ወይም ለመዋለድ አስፈላጊ ከመሆኑ በላይ የወሲብን እርካታዊ ፍላጎት ለማሟላት ሊሆን ይችላል።
 
በ[[ሥነ ሕይወት]] ዘርፍ ሲታይ፣ ወሲብ፣ የእንስትን (ሴትን) እና የተባእትን ([[ወንድ]]ን) ዘር በማዋሃድ ወይንም በማዳቀል፣ ፍጡራንየፍጡራን ዝርያ (species)፣ ከአሮጌ ወደ አዲስ እየታደስ፡ በቅጥልጣይ ረገድ ለረዥም ጊዜ እንዲቆይ የሚያስችል፣ ተፈጥሮ የቸረችው ተፈጥሯዊ ተግባር ነው። በእያንዳንዱ የፍጡር ዝርያ ተባእትና እንስት ፆታዎች ይገኛሉ። እነዚህ ፆታዎች በየራሳቸው ዘርን ማስተላልፍ የሚችሉብት ልዮ የማዳቀያ ህዋሳትን በአካላቸው ወስጥ ይሠራሉ ወይንም ያዘጋጃሉ። [[Image:Sperm-egg.jpg|frame|<big>የተባእት ተስለክላኪ ዘር ህዋስ፣ ከእንስቷ ፍሬ ዘር ህዋስ ጋር፣ በእንስቷ አካል ውስጥ ሲገናኙ:</big>]]እነዚህ ልዮ ህዋሳት 'ጋሜት' (gametes) በመባል ይታወቃሉ። እነዚህ ልዩ ህዋሳት በአካልቸው ተመሳሳይ (በተለይ isogametes በመባል የሚታወቁት) ሊሆኑ ቢችሉም፣ ነገር ግን በአብዛኛው ጊዜ ከተባእትና እንስት የሚገኙት የዘር ህዋሳት በቅርፃቸውም ሆነ በአኳኋናቸው ይለያያሉ። የወንዱ የዘር ህዋስ፣ ም'ጥን ያለና በትንሽ ይዘት ብዙ ዘራዊ ምልክቶችን ማጨቅ እንዲችል ሆኖ የተሠራ ሲሆን፣ ይህንንም ይዞ ረጅም ርቀት መጓዝ እንዲችል የፈሳሽ ውስጥ ተስለክላኪነት ባህርይ ወይንም ችሎታ አለው። የሴቷ ልዩ ህዋስ፣ ከወንዱ ህዋስ ጋር ሲስተያይ በአካሉ አንጋፋ ሲሆን፣ ይህ የሆነበትም ምክንያት ተንቀሳቃሽ ሳይሆን የረጋ ከመሆኑም ሌላ፣ ከተባእት ዘር ጋር ከተገናኘ በኋላ በውስጡ ለሚፈጠረው ሽል አስፈላጊውን የማፋፊያ ንጥረ ነገር መያዝ ስላለበት ነው።
 
የአንድ ፍጡር ፆታ የሚታወቀው በሚፈጥረው የዘር ህዋሥ አይነት ነው። ተባእት ፍጡራን የተባእትን የዘር ህዋሥ (spermatozoa, or sperm) ሲፈጥሩ፣ እንሥት ፍጡራን የእንሥትን የዘር ህዋሥ (ova, or egg cells) ይፈጥራሉ።