ከ«ኒው ዚላንድ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
ሎሌ፦ መያያዣዎች ወደ 189 ልሳናት አሁን በWikidata ገጽ d:q664 ስላሉ ተዛውረዋል።
No edit summary
መስመር፡ 29፦
|የግርጌ_ማስታወሻ =
}}
 
'''ኒው ዚላንድ''' በደቡብ ምዕራብ [[ፓሲፊክ ውቅያኖስ]] የምትገኝ የደሴት ሀገር ናት።
 
==ቋንቋዎች==
 
በኒው ዚላንድ በዋንነት የተነገረው መደበኛ ቋንቋ [[እንግሊዝኛ]] ነው። [[ማዖሪኛ]] በተለይ በ[[ማዖሪ]] ብሔር ይነገራል፣ በ[[1979]] ዓ.ም. ደግሞ ይፋዊ ቋንቋ ሆነ። ከ[[1998]] ዓ.ም. ጀምሮ የአገሩ ሦስተኛው ይፋዊ ቋንቋ [[የኒው ዚላንድ እጅ ምልክት ቋንቋ]] ሆኗል።
 
==ባህል==
 
ከኒው ዚላንድ ሕዝቦች መካከል የማዖሪ ብሔር ከሁሉ ይልቅ ለረጅም ዘመን በደሴቶቹ ላይ ኑረዋል። ማዖሪዎች «[[ሃካ]]» ስለ ተባለው ባህላዊ የውግያ ጭፈራ ታውቀዋል። በኒው ዚላንድ ባሕል ደግሞ የአገሩ [[ስፖርት]] (በተለይ የ[[ራግቢ]]) ቡድኖች ጨዋታ ሳይጀምሩ ሁልጊዜ «[[ሃካ]]» ይጨፍራሉ።
 
አንዳንዴ በቀልድ የኒው ዚላንድ ባህል ዓምዶች «ሦስቱ Rዎች» ይባላሉ - እነሱም «Rugby Racing እና beeR» (ራግቢ፥ እሽቅድድምና [[ቢራ]]) ናቸው። እንዲያውም [[የፈረስ እሽቅድድም]] አሁን እንደ ቀድሞ ደረጃ የተወደደ አልቆየም፣ ራግቢ እና ቢራ ግን ዛሬውንም በኒው ዚላንድ ሕዝብ በኩል በጣም የሚወደዱ ሆነው ቀርተዋል።
 
የኒው ዚላንድ ሰዎች አንዳንዴ በመጫወት ሲሆን በራሳቸውም ሆነ በሌሎች ዘንድ «ኪዊዎች» ይባላሉ። «ኪዊዎች» በተለመደው (በጅምላ አመለካከት) ተጨባጭ ያልሆነ ኀልዮ ወይም አሣብ ሳይሆን ተግባራዊ ጉብዝና እና ሙያ ይመርጣሉ። ኒው ዚላንድ ለረጅም ዘመን በክፍሎች ያልተመደበ ሕብረተሰብ ይቆጠር ነበር - ከሃብታሞችና ደሃዎች ኒው ዚላንድ ኗሪዎች መካከል የነበረው ልዩነት ያንስ ነበር ማለት ነው። በቅርቡ ባለፉት አሥርታት ግን ይሄው ሁናቴ ተቀይሯል።
 
ብዙ የዚው ዚላንድ ኗሪዎች አድገው ወደ ውጭ አገሮች ይጎበኛሉ፣ ብዙዎቹም የባህላዊ ልውውጥ ፕሮግራሞች ይጠቅማሉ፣ ስለዚህ በዓለም ዙሪያ ይገኛሉ፣ በተለይም በ[[አውስትራሊያ]]፣ [[ብሪታንያ]]፣ [[አውሮፓ]]ና [[እስያ]] ይጓዛሉ።
 
{{መዋቅር}}