ከ«ደርግ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
ሎሌ፦ መያያዣዎች ወደ 20 ልሳናት አሁን በWikidata ገጽ d:q828005 ስላሉ ተዛውረዋል።
መስመር፡ 14፦
 
== የደርግ አመሰራረት ==
[[ስዕል:መንግስቱ-ተፈሪ-አጥናፉDerg.gif|250px|thumb|right|የአብዮቱ ዋዜማ መሪዎች፣ [[ሻለቃ መንግስቱ ኃይለ ማርያም]]፣ ብ/ር ጀኔራል [[ተፈሪ በንቲ]]፣ ሊ/ት ኮሎኔል [[አጥናፉ አባተ]]]]
 
ኮ/ል አለም ዘውድ የዘውዱ ተቆርቋሪ እንደሆነ ከታመነበት በኋላ በኮ/ል አጥናፉ አባተ የሚመራ፣ ባብዛኛው ከ[[ሆለታ ጦር ማሰልጠኛ]] የተመረቀ ቡድንና ጥቂት [[የሐረር መኮንኖች ማስለጠኛ]] ምሩቆች ሁነው አክራሪ አብዮተኛ ቡድን መስርተው ከአለም ዘውድ ቡድን ተገንጥለው ወጡ። ይህ ቡድን በኮሚቴ በመዋቀር በአገሪቱ ከሚገኙ 42 የጦር ክፍሎች ሦስት ሦስት ወኪሎች ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ ካደረገ በኋላ ከሰኔ '66 ጀምሮ መደበኛ ስብስባ በማድረግ ''ደርግ''' እንዲቋቋም አደረገ። በአነጋገር ጥንካሬው፣ ውሳኔ ለመወሰን ባለምፍራቱና ባለማመንታቱ ታዋቂነት ያተረፈው [[መንግስቱ ኃይለማርያም]] [[ኢትዮጵያ ትቅደም]] የሚለውን መፈክር ካስተዋወቀ በኋላ በጣም ተቀባይነትን በማግኘቱ የዚሁ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሆኖ ተመረጠ። ኢትዮጵያ ትቅደም የሚለውን መፈክር ባስተዋወቀበት ንግግሩ ኮሚቴው ኢትዮጵያን ከመበታተን አደጋ ለማዳን የቆመ ኃይል አድርጎ በማቅረብ ለተዘበራረቀው አብዮት አቅጣጫ ከመስጠቱም በተጨማሪ የአገሪቱን አንድነት ለማስጠበቅ የሚችል ሃይል ይሄው ኮሚቴ እንደሆነ በማሳየት ለኮሚቴው የሃገር ጠባቂነትን አላማ ለማሰጠት ችሎ ነበር።