ከ«ታላቁ ሳርጎን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 23፦
: ሳርጎን የዓለም ንጉሥ በ34 ውግያዎች አሸናፊ ሆነ፤ እስከ ባህር ዳርቻ ድረስ የከተሞችን ግድግዶች አፈራረሰ። የ[[ሜሉሓ]] መርከቦች፣ የ[[ማጋን]] መርከቦች፣ የ[[ድልሙን]] መርከቦች በአካድ ወደብ አሠረ። ላይኛው አገራት ተሰጠ፦ ማሪ፣ [[ያርሙቲ]]፣ [[ኤብላ]]፣ እስከ አርዘ ሊባኖስ ደን፣ እስከ ብር ተራሮች ድረስ። ሳርጎን ኤንሊል ተፎካካሪ ያልፈቀደለት ንጉሥ፣ ቀን በቀን በፊቱ 5400 ሰዎች ዳቦ እንዲበሉ አደረገ።
: ሳርጎን የዓለም ንጉሥ ኤላምንና [[ማርሐሺ|ፓራሕሱም]]ን አሸነፈ። የሉሒሻን ልጅ ሂሸፕራሺኒ፥ የኤላምን ንጉሥ፥ ማረከው።»
 
በኋላ ዘመን በተጻፈ ሌላ ሰነድ እንደሚለው የሳርጎን መንግሥት ከላይኛ ባሕር ([[ሜዲቴራኒያን]]) ማዶ እስከ አናኪና ካፕታራ ([[ቆጵሮስ]]ና [[ቀርጤስ]]) ድረስ፣ ከታችኛው ባሕር ([[የፋርስ ወሽመጥ]]) ማዶ እስከ ድልሙንና ማጋን ([[ባሕሬን]]ና [[ኦማን]]) ድረስ ተዘረጋ። ሆኖም ከድልሙን በቀር እነዚህ ፉከራዎች በሌላ ምንጭ አልተገኙምና ኣጠራጣሪ ይሆናሉ።
 
ከሳርጎን በፊት የሱመር ይፋዊ እና መደበኛ ቋንቋ ሱመርኛ ሲሆን፣ በአካድ መንግሥት ከሳርጎን ጀምሮ አካድኛ ይፋዊ ሆነ። ይህ የ[[ሴማዊ ቋንቋዎች]] ቤተሠብ አባል ነው። ከዚህ በላይ ለጊዜው በኤላም አካድኛ ይፋዊ ሆኖ እንዳደረገው ይመስላል።