ከ«ታላቁ ሳርጎን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 55፦
 
ከነዚህ ምንጮች፣ የሱመር ዋና ቤተ መቅደስ ከኒፑር ወደ ባቢሎን አዲስ ሥፍራ ስላዛወረው ሕዝቡና ቄሳውንቱ እንዳመጹበት ይመስላል። ከዚህ ዘመን አስቀድሞ «ባቢሎን» ማለት የ[[ኤሪዱ]] መጠሪያ እንደ ነበር የሚል ማስረጃ አለ።<ref>[http://oi.uchicago.edu/pdf/saoc62.pdf "Babylon as a Name for Other Cities..."] p. 25-33. {{en}}</ref>
 
ወደ ምዕራብ ስላደረጉት ዘመቻዎች ሌሎች መዝገቦች ይታወቃሉ። በአንዳንድ ጽላት ዘንድ፣ ሳርጎን የ40 ሺህ ወታደሮች ሠራዊት ነበረው። ከሥራዊቱ ጋር [[ደብረ አማና]]ን ተሻገረ፣ ወደ አርዘ ሊባኖስ ደን ደረሱ። ወደ [[ማርዳማን]] አገር (ከስሜን [[ጤግሮስ]] ምዕራብ የነበረ የ[[ሆራውያን]] ክፍላገር) ለመውረር ያቅዳል። ከዚያ አገር የመጣ ተልእኮ ግን እንዲህ ይጠይቃል፦ «በዳርቻው ክፋቶች የሚያድቡበት የ[[አሞራውያን|አሙሩ]] አገር አይደለምን?» ነገር ግን ሳርጎን አይመልስም፣ የ[[ሲሙሩ]]ም ሰዎችና ከብቶች ሁሉ ይዘው ከተማውን አፈራረሰ። ይህ በስሜን መስጴጦምያ የተገኘ የሆራውያን ከተማ-አገር ነበር። አሙሩ እና [[ሱባርቱ]] አገሮች እንደ ያዙ ይላል።<ref>Joan Goodnick Westenholz, ''Legends of the Kings of Akkad: the Texts'', Text 6, 7.</ref>
 
በአሦርኛው ትውፊት እንደሚለው፣
 
: «ለ[...]4 ዓመታት መንግሥቴን ገዛሁት። የጥቁር ራስ ሕዝብ ላይ ገዛሁት፣ ነገሥኩት፤ ታላላቅ ተራሮች በነሐስ መጥረቢያዎች አጠፋሁ። በላይኛ ተራሮች ወጣሁ፣ በታችኛ ተራሮች በኩል ፈነዳሁ። የባሕሩን አገር ሦስት ጊዜ ወረርሁት፣ ድልሙንን ያዝኩ። ወደ ታላቅ ዱር-ኢሉ ወጣሁ። ... ከኔ በኋላ የሚከበር ማናቸውንም ንጉሥ... የጥቁር ራስ ሕዝብ ላይ ይግዛ፣ ይነግስ። ታላላቅ ተራሮች በነሐስ መጥረቢያዎች ያጥፋቸው፤ በላይኛ ተራሮች ይውጣ፣ በታችኛው ተራሮች በኩል ይፈነዳ፤ የባሕሩን አገር ሦስት ጊዜ ይውረር፤ ድልሙንን ይይዝ፣ ወደ ታላቅ ዱር-ኢሉ ይውጣ።»