ከ«ታላቁ ሳርጎን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 9፦
==ንጉሥ ከመሆኑ በፊት==
 
''የሳርጎን ትውፊት'' በተባለው [[ሱመርኛ]] ጽላት<ref>[http://etcsl.orinst.ox.ac.uk/cgi-bin/etcsl.cgi?text=t.2.1.4# የሳርጎን ትውፊት] {{en}}</ref> የአባቱ ስም [[ላዕቡም]] ይሰጣል። የነገሥታት ዝርዝር የሳርጎን አባት የአጸድ ጠባቂ እንደ ነበር ይለናል። በኋላ ዘመን (7ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ.) በ[[አሦርኛ]] በተጻፈ ትውፊት ዘንድ፣ ሳርጎን «እናቴ ዝቅተኛ ነበረች፤ አባቴንም አላወቅሁም፣ የአባቴም ወንድም በተራራ ይኖራል» ይላል። ግልጽ የሚሆነው ከንጉሣዊ መነሻ አለመሆኑ ነው። የአሦርኛው ሰነድ ደግሞ እንዳለው እናቱ ዲቃላ ማሳደግ ባለመቻሏ በሸምበቆ ቅርጫት ውስጥ በወንዙ ላይ አስቀመጠችውና የመስኖ ቆፋሪ የሆነ ሰው አኪ አገኝቶት አሳደገው። ሳርጎን ያደገበት መንደር «አዙፒራኑ» በ[[ኤፍራጥስ]] ዳር ሲሆን አኪ የአጸዱ ጠባቂ እንዲሆን እንዳስተማረው ይጨምራል።
 
''የሳርጎን ትውፊት'' ንጉሥ ከመሆኑ በፊት ያለውን ታሪክ እንዲህ ይሰጣል። ሳርጎን ከ[[ኪሽ]] ንጉሥ [[ኡር-ዛባባ]] ሎሌዎች መካከል የቤተ መንግሥት አስረካቢ ሲሆን፣ ንጉሡ ኡር-ዛባባ ሕልምን አይቶ ሳርጎንን የ«ዋንጫ ተሸካሚ» ማዕረግ ሾመው፣ ይህም በመጠጦች (ጠጅ) ሳጥን ላይ ሓላፊነቱን ያለው ማለት ነው። ከዚያ ሳርጎን በራሱ ሕልም ኡር-ዛባባ በደም ወንዝ ውስጥ ሲሰመጥ ያያል። ስለዚህ ኡር-ዛባባ ሰምቶ እጅግ ተቸግሮ ሳርጎንን በተንኮል ለመግደል ያቅዳል። ሳርጎን የንጉሥ ተልዕኮ ሆኖ አንድ መልዕክት በጽላት ለ[[ኡሩክ]] ንጉሥ [[ሉጋል-ዛገሢ]] እንዲወስደው አዘዘ። መልዕክቱ ግን መልዕክተኛውን ስለ መግደል የሚል ልመና ነበር። ሰነዱ ተሰብሮ ከዚያ በኋላ ምን እንደ ሆነ ቢያጣም፣ ሳርጎን የአካድ መንግሥት መሥራች ለመሆን ስለ በቃ ሴራው እንዳልተከናወነ መገመት እንችላለን።