ከ«ታላቁ ሳርጎን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 13፦
''የሳርጎን ትውፊት'' ንጉሥ ከመሆኑ በፊት ያለውን ታሪክ እንዲህ ይሰጣል። ሳርጎን ከ[[ኪሽ]] ንጉሥ [[ኡር-ዛባባ]] ሎሌዎች መካከል የቤተ መንግሥት አስረካቢ ሲሆን፣ ንጉሡ ኡር-ዛባባ ሕልምን አይቶ ሳርጎንን የ«ዋንጫ ተሸካሚ» ማዕረግ ሾመው፣ ይህም በመጠጦች (ጠጅ) ሳጥን ላይ ሓላፊነቱን ያለው ማለት ነው። ከዚያ ሳርጎን በራሱ ሕልም ኡር-ዛባባ በደም ወንዝ ውስጥ ሲሰመጥ ያያል። ስለዚህ ኡር-ዛባባ ሰምቶ እጅግ ተቸግሮ ሳርጎንን በተንኮል ለመግደል ያቅዳል። ሳርጎን የንጉሥ ተልዕኮ ሆኖ አንድ መልዕክት በጽላት ለ[[ኡሩክ]] ንጉሥ [[ሉጋል-ዛገሢ]] እንዲወስደው አዘዘ። መልዕክቱ ግን መልዕክተኛውን ስለ መግደል የሚል ልመና ነበር። ሰነዱ ተሰብሮ ከዚያ በኋላ ምን እንደ ሆነ ቢያጣም፣ ሳርጎን የአካድ መንግሥት መሥራች ለመሆን ስለ በቃ ሴራው እንዳልተከናወነ መገመት እንችላለን።
 
''የነገሥታት ዝርዝሩ''ና ''[[የባቢሎን መቅደስ ዜና መዋዕል]]'' (ወይም «የቫይድነር ዜና መዋዕል» <ref>[http://www.livius.org/cg-cm/chronicles/abc19/weidner.html ABC19]</ref>) የተባለው ጽላት ሳርጎን የኡር-ዛባባ «ዋንጫ ተሸካሚ» በማድረጋቸው ከ''ሳርጎን ትውፊት'' ጋራ ይስማማሉ። ዜና መዋዕሉ እንዲህ አለው፦ ''ኡር-ዛባባ ዋንጫ ተሸካሚውን ሳርጎንን የመቅደሱን ወይን ጠጅ መሥዋዕት እንዲቀይር አዘዘው። አልቀየረም ግን ለመቅደሱ ቶሎ እንዲሠዋ ጠነቀቀ።'' ከዚህ በኋላ በአረመኔው ጣኦት ሜሮዳክ ሞገስ የዓለም 4 ሩቦች ግዛት እንዳገኘው በማለት ይጨምራል። ይህ ማለት በ[[ኒፑር]] የነበሩት ቄሳውንት ንጉሥነቱን እንዳዳገፉት ይሆናል።