ከ«ታላቁ ሳርጎን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት
Content deleted Content added
No edit summary |
|||
መስመር፡ 9፦
==ንጉሥ ከመሆኑ በፊት==
''የሳርጎን ትውፊት'' በተባለው [[ሱመርኛ]] ጽላት<ref>[http://etcsl.orinst.ox.ac.uk/cgi-bin/etcsl.cgi?text=t.2.1.4# የሳርጎን ትውፊት] {{en}}</ref> የአባቱ ስም [[ላዕቡም]] ይሰጣል። የነገሥታት ዝርዝር የሳርጎን አባት የአጸድ ጠባቂ እንደ ነበር ይለናል። በኋላ ዘመን (7ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ.) በ[[አሦርኛ]] በተጻፈ ትውፊት ዘንድ፣ ሳርጎን «እናቴ
''የሳርጎን ትውፊት'' ንጉሥ ከመሆኑ በፊት ያለውን ታሪክ እንዲህ ይሰጣል። ሳርጎን ከ[[ኪሽ]] ንጉሥ [[ኡር-ዛባባ]] ሎሌዎች መካከል የቤተ መንግሥት አስረካቢ ሲሆን፣ ንጉሡ ኡር-ዛባባ ሕልምን አይቶ ሳርጎንን የ«ዋንጫ ተሸካሚ» ማዕረግ ሾመው፣ ይህም በመጠጦች (ጠጅ) ሳጥን ላይ ሓላፊነቱን ያለው ማለት ነው። ከዚያ ሳርጎን በራሱ ሕልም ኡር-ዛባባ በደም ወንዝ ውስጥ ሲሰመጥ ያያል። ስለዚህ ኡር-ዛባባ ሰምቶ እጅግ ተቸግሮ ሳርጎንን በተንኮል ለመግደል ያቅዳል። ሳርጎን የንጉሥ ተልዕኮ ሆኖ አንድ መልዕክት በጽላት ለ[[ኡሩክ]] ንጉሥ [[ሉጋል-ዛገሢ]] እንዲወስደው አዘዘ። መልዕክቱ ግን መልዕክተኛውን ስለ መግደል የሚል ልመና ነበር። ሰነዱ ተሰብሮ ከዚያ በኋላ ምን እንደ ሆነ ቢያጣም፣ ሳርጎን የአካድ መንግሥት መሥራች ለመሆን ስለ በቃ ሴራው እንዳልተከናወነ መገመት እንችላለን።
|