ከ«የኢትዮጵያ አየር መንገድ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 33፦
 
'''የኢትዮጵያ አየር መንገድ''' ዋና መሥሪያ ቤቱ በ[[አዲስ አበባ]] [[ኢትዮጵያ]] የሆነ የኢትዮጵያ ብሔራዊ [[አየር መንገድ]] ድርጅት ነው። አየር መንገዱ ከቀድሞው ትራንስ ወርልድ ኤየርዌይስኤይርዌይስ/ Transworld Airways (TWA) ጋር በጋራ የተመሠረተ ሲሆን አስተዳደሩ በአሜሪካኖች እጅ ነበር፤ ድርጅቱ [[ታኅሣሥ ፳፩]] ቀን [[1938|፲፱፻፴፰]] ዓ/ም ተመሥርቶ ለመጀመሪያ ጊዜ ዓለም አቀፍ በረራውን [[መጋቢት ፴]] ቀን [[1938|፲፱፻፴፰]] ዓ/ም ከ[[አዲስ አበባ]] ተነሥቶ [[ካይሮ]] ድረስ አከናወነ።
 
አየር መንገዱ ሲመሠረት ከአሜሪካ ወታደራዊ ኃይል የተገዙና በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ያገለገሉ አምስት ዲ.ሲ. ፫ ([[DC 3-C47]]) አውሮፕላኖች ነበሩት። በዓለም ዙሪያ በ[[አፍሪካ]]፤ በ[[እስያ]]፤ በ[[አውሮፓ]] እና በ[[አሜሪካ]] ክፍለ አህጉራት ወደ ፶ የመንገደኛና የጭነት አገልግሎት ሲሰጥ፤ በሀገር ውስጥ ደግሞ በአሁኑ ጊዜ ፲፮ መድረሻዎችን ያገለግላል። ዋና የጣቢያው ማዕከል በአዲስ አበባ የሚገኘው [[ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ]] ነው።
መስመር፡ 41፦
አየር መንገዱ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ፌደራላዊ መንግሥት የተያዘ የኢትዮጵያውያን ሀብት ሲሆን፤ በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ለሽያጭ እና ለግዢ እንዲሁም ለብድር አመቺ እንዲሆን ተብሎ በአየር መንገዱ ሙሉ ቁጥጥር ሥር በ[[ኬይማን ደሴቶች]] የተመሠረተ ድርጅት ባለቤት ነው።
 
የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ለመንገደኞች አገልግሎት አዲሱንና ዘመናዊውን የቦይንግ ፯፻፹፯ (Boeing 787) ድሪምላይነር አውሮፕላን በማዘዝና ጥቅም ላይ በማዋል ከአፍሪካ የመጀመሪያው አየር መንገድ ሊሆን ነው። የታዘዙትን አሥር ቦይንግ ፯፻፹፯ ድሪምላይነር (Boeing 787 Dreamliner) አውሮፕላኖች እ.አ.አ. በ2009 መጨረሻ ላይ እንደሚረከብና ጥቅም ላይ እንደሚያውል ይጠበቃል። ከዚህ በተጨማሪ አየር መንገዱ 8 ቕ400 አውሮፕላኖች ከቦምባርዲየር (''Bombardier'' ለሀገር ውስጥ መንገደኞት አገልግሎት አዟል።
 
በ[[1989|፲፱፻፹፱]] ዓ.ም. ዓለማየሁ በቀለ በላይነህ፣ ማትያስ ሰሎሞን በላይ እና ሱልጣን አሊ ሁሴን የተባሉ ሦስት ኢትዮጵያውያን፣ ከአዲስ አበባ ተነስቶ በ[[ናይሮቢ]] በኩል ወደ [[ቦምቤይ]] በረራ ላይ የነበረውን [[የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ 961|የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ በረራ ቁ. ፱፻፷፩]] በዓየር ላይ ጠለፉ። በጠላፊዎቹም ትእዛዝ ወደ [[አውስትራሊያ]] ሲያመራ ነዳጅ በመጨረሱ ምክንያት በረራው በ[[ሕንድ ውቅያኖስ]] ላይ ወደምትገኘው [[ኮሞሮስ|የቆሞሮስ ደሴት]] ተጠግቶ ከደሴቷ ግማሽ ኪሎሜትር ውቅያኖሱ ላይ ሊያርፍ ሲሞክር የዓየር ተሽከርካሪው ተሰባብሮ ፈነዳ። ከመንገደኖቹም ውስጥ፣ ጠላፊዎቹን ጨምሮ መቶ ሃያ ሦሥት ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። ከሞቱት መንገደኞች አንዱ፣ ኬንያዊው የፎቶ-ጋዜጠኛ [[ሞሐመድ አሚን]] ነበር።
 
[[የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ 409|የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ፬፻፱]] ጥር ፲፯ ቀን ፳፻፪ ዓ/ም ከተነሳከቤይሩት በተነሳ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ባልታወቀ አደጋ ምክንያት በ[[ሜድትራኒያን ባሕር]] ላይ ውድቆ የሰመጠ በረራ ነበር።
== ደግሞ ይዩ ==
* [[የኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋዎች]]