ከ«ቅኔ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 1፦
፮፮
 
'ቅኔ'፡ማለት፡'ቀነየ'፡ገዛ፡ካለው፡ግስ፡የተገኘ፡ጥሬ፡ዘር፡ነው።ወይም፡'ቀነየ'፡ገዛ፡የ ሚለውን፡አንቀጽ፡ያስገኘ፡ጥሬ፡ዘር፡ነው።ፍችውም፡'መገዛት'፡ማለት፡ነው።'ቁሙ፡እንከ፡ ወኢትሑሩ፡ዳግመ፡ውስተ፡አርዑተ፡ቅኔ'፡እንዲል፡(ገላ.፥5፥1)፥ቅኔ፡ማለት፡መገዛት፡ማለት፡ከኾነ፥ይህ፡ከያንዳንዱ፡ሰው፡በየጊዜው፡የሚመነጨው፡እ ንግዳ፡ድርሰት፡ስለ፡ምን፡ቅኔ፡ተባለ፡ቢሉ፥ፍጡር፡ዐዲስ፡ዐዲስ፡ምስጋና፡እየደረሰ፡በ ማቅረብ፥ለፈጣሪው፡መገዛቱን፡የሚገልጥበት፡ስለ፡ኾነ፡ነው።ለፍጡራን፡የሚደረሰውም፡ቅ ኔ፥ቅኔው፡የሚደረስለት፡ፍጡር፡ከቅኔ፡ደራሲው፡በላይ፡ክብር፡ያለው፡መኾኑን፡የሚገልጽ ፡ድርሰት፡ስለ፡ኾነ፥መገዛትን፡ከማመልከት፡የራቀ፡አይደለም።
አንድም፥ሕዋሳተ፡አፍኣን፣ሕዋሳተ፡ውስጥን፡ለኅሊና፡አስገዝቶ፥በተወሰነ፡ቍርጥ፡ሐሳብ ፡የሚታሰብ፡ስለ፡ኾነ፥ቅኔ፡ተብሏል።ይኸውም፡ሊታወቅ፥በቅኔ፡ምስጢር፡ልቡ፡የተነካ፡ሰ ው፥ቅኔ፡በሚያስብበት፡ጊዜ፥እፊቱ፡የሚደረገውን፡ነገር፡እያየ፣እየሰማ፥አይሰማም።ከዚ ህም፡የተነሣ፥በጎንደሮች፡መንግሥት፥የቍስቋሙ፡አለቃ፡በእልፍኙ፡ውስጥ፡ምንጣፉን፡አስ ነጥፎ፥መጻሕፍቱን፡እፊቱ፡ደርድሮ፥ለበዓለ፡ቍስቋም፡የሚቀኘውን፡ቅኔ፡ሲያወጣና፡ሲያወ ርድ፥ንጉሡ፡ዘው፡ብለው፡ቢገቡ፥ልቡ፡ተመሥጦ፥ሊያያቸው፡ባለመቻሉ፥ቀና፡ብሎ፡ሳያያቸው ፡ቁጭ፡እንዳለ፡ቀረ።ንጉሡም፥ነገሩ፡ደንቋቸው፥ፍጻሜውን፡ለማየት፥ርሱን፡ዐልፈው፡ዐል ጋ፡ላይ፡ተቀምጠው፥ኹኔታውን፡ይመለከቱ፡ዠመር።
ከ «https://am.wikipedia.org/wiki/ቅኔ» የተወሰደ