ከ«ዓፄ ዘርአ ያዕቆብ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 27፦
ዓፄ ዘርአ ያእቆብ ንጉስ ከሆኑ በኋላ [[ንግስት እሌኒ]]ን በ1434 አገቡ፣ ከዚያም በ1436 ዘውዳቸውን ጫኑ። [[ንግስት እሌኒ]] የ[[ሀድያ]] ንጉስ ልጅ ስትሆን በህጻንነቱዋ የ[[እስልምና]] ተከታይ የነበረች ቢሆንም በጋብቻው ወቅት ክርስቲያን ሆናለች።
 
በ1442 በሰንበት ላይ ተነስቶ የነበረውን የቤ/ክርስቲያን ክፍፍል ለማብረድ ቢችሉም እስከ 1450 ነገሩ ሲሰክን ቆይቱ በ[[ደብረ ምጥማቅ ጉባኤ]] (ተጉለት) ፣ የግብጾቹ ጳጳሳተ በተገኙበት ችግሩን ሊፈቱ ችለዋል ። ሌላው በዘመናቸው የተከሰተው ሃይማኖታዊ ንቅናቄ የደቀ እስጢፋ ወገኖች እምነት ነው። እነዚህ እስጢፋኖስ የተባለ መነኩሴን ትምህርት የተቀበሉ በወንጌል ትምህርት የጸኑ ሰዎች ገዳም ሲሆን በአዲስ ኪዳን እንደተጻፈው በክርስቶስ ማመን እንጂ ለመስቀል መስገድና ለስእል መስገድ ለንጉሥም እንደ መለኮት መስገድ አይገባም የሚሉ ነበሩ። በማለታቸውም አፍንጫቸውና ምላሳቸው እየተቆረጠ፣ የከብት አጎዳ እየተነዳባቸው የተገደሉት ብዙ ናቸው። አስተማሪያቸው እስጢፋኖስም ተሰቃይቶ ተገድሎአል።
 
በ1445 እና ከዚያ በኋላ በተነሱ ጦርነቶች ላይ በመሳተፍ ሁሉን በድል በማጠናቀው ግዛታቸውን ያሁኒቷን ሶማልያን ሁሉ ያቅፍ ነበር።