ከ«የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 11፦
 
[[ስዕል:የደራስያን ቴምብር.jpg|right|thumb]]
ኢ.ደ.ማ. ካከወናቸው ዐበይት ተግባራት አንዱ በ[[2002|፳፻፪]] ዓ/ም የተከበረውን የ፶ኛ ዓመት የወርቅ በዓል አጋጣሚ በማድረግና [[የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት]]ን በማስተባበር በ[[ሀዲስ አለማየሁ]] ፣ በ[[ከበደ ሚካኤል]] ፣ በሎሬት [[ጸጋዬ ገብረ መድህን]] እና በ[[ስንዱ ገብሩ]] ምስል ያሳተማቸው የመታሠቢያ ቴምብሮች አንዱ ነው። በዚህ ትብብር “የኢትዮጵያ ደራስያን ፪ኛ ዕትም” በሚል የታተሙትና [[ጳጉሜ ፪]] ቀን [[2004|፳፻፬]] ዓ/ም በ[[አዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ]] የተመረቁት ቴምብሮች ደግም ደራስያን ነጋድራስ[[አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ]]፣ ቀኝ-ጌታ [[ዮፍታሔዮፍታሄ ንጉሤ]፣ [[ኅሩይ ወልደ ሥላሴ (ብላቴን ጌታ)|ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ]] እና አቶ [[ተመስገን ገብሬ]] ናቸው። የቴምብሮቹ ምስሎች የተነደፉት በአገኘሁ አዳነና እሸቱ ጥሩነህ ሲሆን፤ የ፳ ሳንቲም፣ የ፹ ሳንቲም፣ የአንድና ሁለት ብር ዋጋ አላቸው። <ref> ‘ሪፖርተር’ Ethiopian Reporter, “የአራት ደራስያን መታሰቢያ ቴምብሮች ታተሙ” 09 SEPTEMBER 2012 </ref> እነዚህ አንጋፋ ደራሲያን በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሥነ ጽሑፍ ታሪክ ውስጥ ጉልህ እና ዘላለማዊ አሻራ የተዉ ናቸው፡፡
 
የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር በግማሽ ምዕተ ዓመት ሕይወቱ ጊዜያት በርካታ ውጣ ውረዶችን አሳልፏል። አቋሙ ዘለቄታ ባለው መልክ እንዲቀጥል ለማድረግ የመጀመርያው ፕሬዝዳንት የነበሩት የ“አርዐያ” እና “የኤደኑ ጃንደረባ” መጻሕፍት ደራሲ [[ግርማቸው ተክለ ሐዋርያት]] በጊዜው በብሔራዊ ቴአትር ለተወሰነ ጊዜ ከታየው “ቴዎድሮስ” ከተሰኘው ተውኔታቸው ገቢ ላይ ፲ሺ ብር ለማኅበሩ ለግሰው እንደነበር ተዘግቧል። ሆኖም፣ ማኅበሩ በገንዘብ አቅሙ የጠነከረ ስላልነበረ በተለያዩ ጊዜያት የሥራ ክንውኑን ያልቀለጠፈ እንዳደረገው ይነገራል። ደራሲ ማሞ ውድነህ ፕሬዝዳንት በነበሩበት ወቅት የአባላቱ ቁጥር አነስተኛነትና የገቢ ምንጮቹ ደካማነት የጽሕፈት ቤቱን የቤት ኪራይ እንኳን በአግባቡ እንዳይከፍል እስከማድረግ ደርሶ ነበር።