ከ«የኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 10፦
በማኅበሩ የሥራ ደንብ፣ የአንድ ደራሲ ረቂቅ የገምጋሚ ኮሚቴውን ምዘና አልፎ፤ አርትኦቱ ተሠርቶ እና ታትሞ ለገበያ ከቀረበ በኋላ ከሚያገኘው ትርፍ ላይ የአርትኦት ክፍሎ፣ ለማተሚያ ቤቱ እና ለኢትዮጵያ ደራስያን ማኅበር የተወሰነ ክፍያ የማድረግ ግዴታ ይኖርበታል።
 
[[ስዕል:የደራስያን ቴምብር.jpg|right|thumb]]
ኢ.ደ.ማ. ካከወናቸው ዐበይት ተግባራት አንዱ በ[[2002|፳፻፪]] ዓ/ም የተከበረውን የ፶ኛ ዓመት የወርቅ በዓል አጋጣሚ በማድረግና [[የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት]]ን በማስተባበር በ[[ሀዲስ አለማየሁ]] ፣ በ[[ከበደ ሚካኤል]] ፣ በሎሬት [[ጸጋዬ ገብረ መድህን]] እና በ[[ስንዱ ገብሩ]] ምስል ያሳተማቸው የመታሠቢያ ቴምብሮች አንዱ ነው። በዚህ ትብብር “የኢትዮጵያ ደራስያን ፪ኛ ዕትም” በሚል የታተሙትና [[ጳጉሜ ፪]] ቀን [[2004|፳፻፬]] ዓ/ም በ[[አዲስ አበባ ቴአትርና ባህል አዳራሽ]] የተመረቁት ቴምብሮች ደግም ደራስያን ነጋድራስ[[አፈወርቅ ገብረ ኢየሱስ]]፣ ቀኝ-ጌታ [[ዮፍታሔ ንጉሤ]፣ [[ኅሩይ ወልደ ሥላሴ (ብላቴን ጌታ)|ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ]] እና አቶ [[ተመስገን ገብሬ]] ናቸው። የቴምብሮቹ ምስሎች የተነደፉት በአገኘሁ አዳነና እሸቱ ጥሩነህ ሲሆን፤ የ፳ ሳንቲም፣ የ፹ ሳንቲም፣ የአንድና ሁለት ብር ዋጋ አላቸው። <ref> ‘ሪፖርተር’ Ethiopian Reporter, “የአራት ደራስያን መታሰቢያ ቴምብሮች ታተሙ” 09 SEPTEMBER 2012 </ref> እነዚህ አንጋፋ ደራሲያን በኢትዮጵያ ዘመናዊ ሥነ ጽሑፍ ታሪክ ውስጥ ጉልህ እና ዘላለማዊ አሻራ የተዉ ናቸው፡፡