ከ«ሶቪዬት ሕብረት» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
መስመር፡ 41፦
s1 = ሩሲያ|
s1_ባንዲራ = Flag_of_Russia_1991-1993.svg|
s2 = ጆርጂያጂዮርጂያ|
s2_ባንዲራ = Flag_of_Georgia_(1990-2004).svg|
s3 = ዩክሬይን|
መስመር፡ 69፦
s15 = ሊትዌኒያ|
s15_ባንዲራ = Flag_of_Lithuania_1989-2004.svg
}}
}}'''ሶቭየት ሕብረት ሰብአዊ ሪፐብሊክ''' በ[[1910|፲፱፻፲]] ዓ.ም. የተከሰተውን የ[[ሩሲያ አብዮት]] ፍንዳታ፤ እንዲሁም ያንን ተከትሎ ለሦስት ዓመታት የተከናወነውን የሩሲያ «ውስጣዊ ሕዝባዊ የርስ በርስ ግጭት» ተከትሎ በስብአዊ ሕገ መንግሥት (socialist constitution) በአራት ሪፑብሊኮች ቅንብርነት የተመሠረተ አገር ነበር።
 
በ[[ሁለተኛው የዓለም ጦርነት]] ፍጻሜ ከቀድሞው የ[[ናዚ ጀርመን]] እጅ የተወሰዱ አገሮችን በማቀላቀል እንዲሁም በ[[1949|፲፱፻፵፱]] ዓ.ም በጉልበት ሌሎች የምሥራቅ [[አውሮፓ]] አገሮችን በመቀላቀል ሕብረቱ አሥራ ስድስት ሪፑብሊኮችን ያካተተ ነበር። በዘመን ቆይታና በጥንካሬም የጎለበተ ሕዝባዊ ዓብዮታዊ የሕብረት ሪፑብሊክ በመሆኑም በተለይ በ«ቀዝቃዛ ጦርነት» (cold war) በሚባለው በ«ምዕራብና በምሥራቅ» ዓለም ተከስቶ በነበረው ፍጥጫ ጊዜ፣ በዓለም ላይ ለሚመሠረቱ ሕዝባዊ መንግሥታት ዋና የ[[ሽከታ]] አርአያ የነበረ መንግሥት ነበር።
Line 77 ⟶ 78:
በሕዝባዊ አብዮታዊ እንቅስቃሴ መነሻነት በኃይልና በፖለቲካ ሚዛናት በሰባ ዓመታት ውስጥ ዳብሮ በዓለም ከሁለቱ ኃያላን መንግሥታት አንዱ እስከመሆን የደረሰው የሶቪየት ሕብረት በዕድሜው መግቻ ዓመታት ላይ በዓለም የተከሰቱ ሁለት ዓቢይ ጉዳዮች ለፍጻሜው ዋና ምክንያቶች እንደነበሩ ይገለጻል።
 
ኬኔዝ ኤስ ዴፊይስ (Kenneth S. Deffeyes) “Beyond Oil” ላይ እንዳሰፈረው አንደኛው፤ የ[[አሜሪካ]]ው ፕሬዚደንት [[ሮናልድ ሬጋን]] [[ሳውዲ አራቢያ]] የነዳጅ ዋጋዋን እንድታወርድ በማበረታታቸው የሶቪዬት ሕብረት ከነዳጅ ሽያጥ የምታገኘውን ትርፍና የውጭ ምንዛሪ መጠን ክፉኛ ማመንመኑ፤<ref>Kenneth S. Deffeyes, Beyond Oil: The View from Hubbert's Peak.</ref> ሁለተኛ በሶቪዬት ሕብረት ሥልጣንን የተረከቡት [[ሚካይል ጎርባቾቭ]] በአገሪቱ ዱኛ <ref name="መስፍን አረጋ">[[መስፍን አረጋ (ዲባቶ)]]፣ "[[ሰገላዊ አማርኛ]]"፤፳፻ ዓ.ም.</ref>(economy) እንዲሁም የኮሙኒስት አመራር ላይ ጥልቅ የሆኑ [[ፔሬስትሮይካ]] እና [[ግላስኖስት]] በሚል ስያሜ የሚታወቁትን ሁለት ሥር ነቅናቂ ለውጦችን መትግበራቸው ነው።
 
ለምሳሌ የጎርባቾቭ የግላስኖስት ውጅማ <ref>[[ name="መስፍን አረጋ (ዲባቶ)]]፣ "[[ሰገላዊ አማርኛ]]"፤፳፻ ዓ.ም</ref>(policy)፣ ከዚህ በፊት በአስተዳደሩ መሣሪያዎች ከሕዝቡ በምስጢርነት ይደበቁ የነበሩ መንግሥታዊ/ሰብአዊ፤ ወ.ዘ.ተ. መረጃዎችን ማንኛውም ዜጋ የማግኘት መብቱን ያረጋገጠለት አቢይ ውጅማ ሲሆን፤ የፔሬስትሮይካ ስልት ደግሞ ከአብዮቱ ጀምሮ የማዕከላዊው የኮሙኒስት ሸንጎ በቁልፍ እጅ ይዞት የነበረውን ስልጣን በማላቀቅ የቻራስፍና (democracy) ስርዐት በሕዝቡ አዕምሮ እንዲሰነጽ መንገድ የከፈተ ውጅማ ነው።
 
የቀድሞው የሶቪዬት ሕብረት መጨረሻ ላይ [[ታኅሣሥ 16|ታሕሣሥ ፲፮]] ቀን ፲፱፻፹፬ ዓ.ም ተደምስሶ በዓለም መንግሥታት እውቀትና ስምምነት ህጋዊ ወራሽነት የ[[ሩሲያ]] መንግሥት እንደሆነ ታወጀ። ሩሲያም በዚህ መሠረት የቀድሞውን የሶቪዬት ሕብረት የውጭ ዕዳዎች እንዲሁም የውጭ ንብረቶች በፈቃዱ ተቀበለ። በቀድሞው የሶቪዬት ሕብረት ተፈርመው የነበሩም ዓለም አቀፍ ስምምነቶችንም ሩሲያ መቀበሏን አስታውቃለች።