ከ«የዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ድምፅ መልዕክት ወደ ንግሥት ቪክቶሪያ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

no edit summary
'''የዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ ድምፅ መልዕክት ወደ ንግሥት ቪክቶሪያ''' በ[[1891|፲፰፻፺፩]] ዓ.ም. [[ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ]] ለእንግሊዟ [[ንግሥት ቪክቶሪያ]] በ[[ፎኖግራፍ]] ድምፅ መቅርጫ አድርገው የላኩት የድምፅ ደብዳቤ ነበር<ref>http://paperspast.natlib.govt.nz/cgi-bin/paperspast?a=d&d=HBH18990331.2.38</ref>። ደብዳቤው በሰላምታና በመልካም ምኞት ላይ ሲያተኩር፣ እንዲሁም በቅርቡ የተካሄደውን የ[[እንግሊዝ]]ን በ[[ሱዳን]] ላይ ድል በማስመልከት የ[[መተማ]] ከተማ የኢትዮጵያ እንደሆነ ንግሥቲቱ እንዲወስኑ ያሳውቃል። ከጎን ፋይሉ ቀርቧል። ከዚህ በታች ደግሞ መልዕክቱ ቃል በቃል ምን እንደሚል በጽሑፍ ቀርቧል።

«እኔ ዳግማዊ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ እጅግ ለከበሩ ወዳጃችን ቪክቶሪያ የታላቅ የእንግሊዝ ሕዝብ የሕዝብ ነገሥታት መድኃኔ ዓለም ጤና ይስጥልኝ እላለሁ :: እላለሁ።

በሙሴ ሃሪንግቶን እጅ እጅግ የተዋበ ያማረ የንግሥት ፎኖግራፍ ሲደርስልኝ የከበሩ ንግሥት ድምፅ አጠገቤ ሆነው ስሰማ በብዙ ደስታ አደመጥኩ :: አደመጥኩ።

ለኛና ለመንግሥቴ ስለ መልካም ምኞትዎ እግዚአብሔር ያመስግንዎ ::ያመስግንዎ። ለርስዎ ዕድሜና ጤና ለሕዝብዎ ሰላምና ዕረፍት እግዚአብሔር ይስጥዎ ::ይስጥዎ። በሁለታችን ሕዝብ መካከል ያለውን ጉዳይ ሁሉ ከሙሴ ሃሪንግቶን ጋር ተነጋገርኩ ::ተነጋገርኩ። እርሱም አሁን ወደ እንግሊዝ አገር እመለሳለሁ ቢለኝ ጉዳያችንን ሁሉ አቃንተህ ብትመለስ ደስ ይለኛል ብዬ ነገርኩት ::ነገርኩት። አሁን ደግሞ ንግሥት በደህና እንዲቀበሉት :: እንዲቀበሉት።

ደግሞ የመተማ ነገር የእኛ ታላቁ ንጉሣችንና ብዙ የአገራችን ሰዎች ስለኃይማኖታቸው እልህ ብለው የሞቱበትን ለሙሴ ሃሪንግቶን ነግረነዋልና ይህንን ከተማ የእንግሊዝ መንግሥት እንዲያውቅልን እርስዎ ይረዱናል ብዬ ተስፋ አለኝ :: አለኝ።

ኢትዮጵያ እና የእንግሊዝ አገር በሰላምና በፍቅር እንዲኖሩ እግዚአብሔር ይርዳን ብዬ ለታላቅ ሕዝብዎ የክብር ሰላምታዬን አቀርባለሁ :: አቀርባለሁ።»

==ማጣቀሻ ==
6,498

edits