ከ«ደጃዝማች ኪዳኔ ወልደመድኅን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
ትሩ፡ ነው፡ ደጀን፡ የሚለውን፡ ደጀኒ፡ አድርጊዋለሁ፡ መቺ፡ ነው፡ ደጃዝማች፡ የተባሉት? ቦረና፡ አልገዙም፡ ወይ?
መስመር፡ 1፦
[[Image:Kidane Aba Kesto.jpg|thumb|300px|ደጃ/ኪዳኔ በአርበኝነት]]
 
'''ኪዳኔ ወልደመድኅን''' ዓርብ ሌሊት [[ሐምሌ 2|ሐምሌ ፪]] ቀን [[1907|፲፱፻፯]] ዓ.ም [[ቡልጋ]] በ[[ከሰም ]]ወረዳ፤ [[የለጥ]] ቀበሌ፤ ልዩ ስሙ ቡሄ አምባ በሚባለው ሥፍራ ላይ ከናታቸው ከወይዘሮ አስካለ ደጀንደጀኔ እና ከአባታቸው ከቀኛዝማች ወልደመድኅን አዩደረስ ተወልደው [[ነሐሴ 10|ነሐሴ ፲]] ቀን በጥምቀት ስም ኪዳነ ማርያም ተሰይመው [[የለጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ]][[ ቤተ ክርስቲያን]] [[ክርስትና]] ተነሱ። አባታችው ቀኛዝማች ወልደመድኅን ትውልድ ሃገራቸው [[ወበሪ]] ሲሆን፤ በዘመኑ የታወቁ ስመጥሩ ጠበቃ ነበሩ። ከወይዘሮ አስካለም ጋር የተገናኙት ሁለቱም እወረዳው ፍርድ ቤት [[ኮረማሽ]] ለየጉዳያቸው ሄደው እንደነበር ይነገራል። ኪዳነማርያምም እስከ ፲፪ ዓመት እድሜያቸው እዚያው ቡሄ አምባ ከአያታቸው አቶ ደጀንደጀኒ ደብሩ ቤት እንዳደጉና የቄስ ትምህርት ቤት ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን እንደተከታተሉ ተጽፏል። ከዚህ በኋላ አባታቸው ቤት እያደጉ የ[[አማርኛ]]ና የ[[ግእዝ]] ትምህርት አጠናቀዋል።
 
አካለ መጠን ሲደርሱ በ፲፰ዓ መታቸው በ[[1925|፲፱፻፳፭]] ዓ.ም. [[አዲስ አበባ]] በ[[ክብር ዘበኛ]] ደንብ ተቀጥረው ወዲያው በ[[ቀኅሥ|ንጉሠ ነገሥቱ]] ትዕዛዝ ከስድሳ ዘጠኝ አዲስ ወታደሮች ጋር [[ባሌ]] ተመድበው እስከ [[1927|፲፱፻፳፯]] ዓ.ም ድረስ በተራ ወታደርነት ከዚያም በ ሃምሳ ዓለቃና በባሻነት ማእረግ ሲያገለግሉ ከቆዩ በኋላ [[ኢጣሊያ]] [[ኢትዮጵያ]]ን ሊወር ሲመጣ በ[[1928|፲፱፻፳፰]] ዓ.ም በምስራቅ ደቡብ በ[[ደጃዝማች በየነ መርዕድ]] እና በ[[ጄነራል አስፋው ወልደ ጊዮርጊስ]] መሪነት፤ የመጀመሪያ ልጃቸው ዓለማየሁ በተወለደ በዘጠኝ ቀኑ፤ [[ጥቅምት 11|ጥቅምት ፲፩]] ቀን [[1928|፲፱፻፳፰]] ዓ.ም ከ[[ጎባ]] ወደ [[ኦጋዴን]] ዘመቱ።