ከ«ናርመር» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
r2.7.1) (ሎሌ መጨመር: fa:نارمر
Robot: de:Narmer is a good article; cosmetic changes
መስመር፡ 1፦
[[ስዕል:Catfish-chisel.gif|thumb|300px|የናርመር (አምባዛ-መሮ) ምልክት በዝሆን ጥርስ]]
'''ናርመር''' ለ[[ሥነ ቅርስ]] የሚታወቅ [[የግብጽ የቀድሞ ዘመነ መንግሥት]] ፈርዖን ነበረ። ስሙ በ[[ግብጽ ሃይሮግሊፍ]] ሲጻፍ፣ የ[[አምባዛ]] (አስቀያሚ የባሕር [[አሳ]] ወይም በ[[ግብጽኛ]] «ናር») ከ[[መሮ]] (በግብጽኛ «መር») በላይ ነው። ከ[[ሔሩ]] (ወይም ሆሩስ፣ ሖር) ወገን በመሆኑ ስሙ በሙሉ «ሔሩ ናር-መር» (ወይም ምናልባት «ሔሩ መር-ናር») ነበረ።
 
[[ስዕል:Dula.jpg|thumb|left|250px|የናርመር ዱላ ትርዒት]]
[[የናርመር ዱላ]] የተባለው ቅርስ በዙፋን ሲቀመጥ የታችኛ (ስሜኑ) ግብጽ ዘውድ በራሱ ላይ ሲጫን ያሳያል። በሱም ዙሪያ የሚያገልግሉ ሰዎች አሉ። በላይኛው ተርታ አጫጭር ሰዎች ዓላማዎች ሲሸክሙ አንዱ «[[ሴት (ግብፅ)|ሴት]]» ምልክት ([[አዋልደጌስ]] ወይም [[ቀበሮ]])፣ አንዱም የ[[ጊንጥ]] ምልክት፣ ሁለቱም የሔሩ ምልክት ([[ጭላት]]) አለባቸው።
 
በ[[1890]] ዓ.ም. በተገኘው [[የናርመር መኳያ ሠሌዳ]] በተባለው ቅርስ ላይ የናርመር መልክ በሁለቱ ገጾች ላይ ይታያል። በፊተኛው ገጽ ላይ የታችኛ ግብጽ ዘውድ (ቀዩ ዘውድ)፤ በጀርባውም ላይ የላይኛ ግብጽ ዘውድ (ነጩ ዘውድ) በራሱ ላይ ይታያል። ስለዚህ ሁለቱ ክፍሎች መጀመርያው ያዋሐደው ፈርዖን በተለመደው ታሪክ [[ሜኒስ]] ሲሆን፣ እርሱና ናርመር አንድ እንደ ነበሩ በሰፊ ይታመናል።
 
ቀዩ ዘውድ ባለበት ገጽ ላይ እንደ ተለመደው አጫጭር ሰዎች ያገልግሉታል። ባንዱ አገልጋይ አጠገብ ሁለት ሃይሮግሊፎች «ጨቲ» (ወይም አማካሪ) ይላሉ። በግብጽ ሥነ ቅርስ እስከሚታወቅ ድረስ የሃይሮግሊፍ አጠራር እንደ ድምጽ ፊደል<hiero> V13 t</hiero>(ጭ፣ ት ) ሲጠቀም መጀመርያው ግዜ ይህ ነው። ይህም የሚያሳየን፣ ሃይሮግሊፍ እንደ ፊደል መጠቀሙን በዚሁ ዘመነ መንግሥት አዲስ የተማረ ነገር መሆኑ ነው። ከዚህም በታች 2 [[ዘንዶ-ነብር]] በሠሌዳው ይታያል።
መስመር፡ 12፦
 
[[መደብ:ፈርዖን]]
 
{{Link GA|de}}
 
[[ar:نارمر]]