ከ«የብርሃን መጠላለፍ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
r2.7.3) (ሎሌ ማስተካከል: uk:Інтерференція хвиль
Robot: zh:干涉 (物理学) is a featured article; cosmetic changes
መስመር፡ 1፦
[[Fileስዕል:Ebohr1.svg|left|thumb|200px| [[ቶማስ ያንግ]] የ[[ብርሃን ውልግደት]]ን በሁለት በተሸነተሩ ካርዶች አማካይነት ለማሳየት ያደረገው ሙከራ። ይህ የያንግ [[ሙከራ]] ብርሃን ሞገድ እንዳለው ያረጋገጠ ነበር።]]
[[የብርሃን መጠላለፍ]] እንደማንኛውም [[ሞገድ]] መጠላለፍ ነው እንጂ ልዩ አይደለም። ለምሳሌ አንድ የረጋ ውሃ ላይ ሁለት ልጆች የተለያየ ቦታ ላይ ጠጠር ቢጥሉ፣ ከጠጠሮቹ እየከበቡ የሚሰፉት ሞገዶች የሚሰሩት መጠላለፍ አንድ ቦታ በሃይል እንዲጎብጡ፣ ሌላ ቦታ እንዲያንሱ እያደረገ ለአይን የሚስብ የመጠላለፍ ቅርጾች በውሃው ገጽታ ላይ ይሰራሉ። ብርሃንም እንዲህ አይነት የመጠላለፍ ባህርይ ያሳያል። ጉዳዩን በቀላሉ ለማየት የ[[ያንግን ሙከራ]] ማካሄድ ይረዳል። የያንግ ሙከራ ምንድን ነው፣ አንድ አይነት ቀለም ያለው ብርሃን አንድ በቀጭኑ የተሸነተረ ካርድ ላይ ይብራል። ከዚህ ሽንትር ካርድ ብርሃኑ [[የብርሃን መወላገድ|እየተወላገደ]] ይሄድና ሌላ ሁለት ቦታ ላይ የተሸነተረ ካርድ ላይ እንዲያርፍ ይደረጋል። ከኒህ ሁለት ሽንትሮች ያመለጠው ሁለት ጊዜ የተወላገደ ብርሃን ንጹህ ግድግዳ ላይ እንዲያርፍ ይደረጋል። የብርሃንን መጠላለፍ በደንብ በሚያሳይ መልኩ ይህ የሚያርፈው ብርሃን ብዙ ደማቅና ጨለማ ሸንተረሮች በግድግዳው ላይ ይፈጥራሉ። ከዚህ በተረፈ የብርሃን መጠላለፍ በተፈጥሮም እንዳለ ለማስተዋል ይቻልል። ለምሳሌ ሥሥ የዘይት ወይም ቤንዚን እድፍ በውሃ ላይ ተንጣሎ ሲገኝ የሚፈጥረው ኅብረ ቀለም ከብርሃን መጠላለፍ የሚመጣ ነው። የ[[ሲዲ]] ገጽታም ኅብረ ቀለም ማሳየቱ ብርሃን መጠላለፍ የሚመነጭ ነው።
 
[[መደብ: ብርሃን]]
 
{{Link FA|zh}}
 
[[ar:تداخل (فيزياء)]]