ከ«ደርግ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
r2.7.3) (ሎሌ መጨመር: bg:Дерг
www. የአብዮቱ ዋዜማ.com/amharic
መስመር፡ 11፦
ሥርዓቱ በሁለት ተጻራሪ አጣብቂኞች ውስጥ ገብቶ ባለበት በዚህ ወቅት በተፈጠረ የርሃብ፣ የኑሮ ውድነት፣ ሙስናና አጠቃላይ ቅሬታ የ[[1966]]ቱ አብዮት እንዲፈነዳ ግድ ሆነ። አብዮቱን ሀ ብሎ የጀመረው የ[[ወታደር|ወታደሩ]] መደብ ሲሆን፣ ጥር፣1966 ዓ.ም. [[ነገሌ]]፣ [[ሲዳሞ]] ላይ ሰፍሮ የነበረው የ[[ምድር ጦር]] ሠራዊት አዛዥ መኮንኖቻቸውን ሲያግቱ ይጀምራል። ጉዳዩ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በሚኖሩ የሰራዊቱ ክፍሎች ድጋፍን በማግኘቱ በወታደሩ መደብ ከመዛመቱም ባሻገር ወደ ተቀረው ዜጋም በመዝለል በመጋባቱ በብዙ ከተማዎች አመጽ መነሳት ጀመረ።
 
የዘውዱ መንግስት ለዚህ መልስ ይሆናል ብሎ ያስበውን ብዙ ጥቃቅን ለውጦችን አድርጓል፤ ለምሳሌ አክሊሉ ሃብተወልድን አንስቶ [[እንዳልካቸው መኮንን]]ን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጓል፣ ለወታደሩ ልዩ ደመዎዝ ጭማሪ አድርጓል፣ ሊተገበር የነበር የትምህርት ስርዓት ማሻሻያ ለውጥን በተነሳበት ተቃውሞ ምክንያት አስቁሟል፣ የካቲት ወር ላይ እንዲሁ የ1947ቱን [[ሕገ መንግስት]] ለማሻሻል ሞክሯል። ምንም እንኳ እኒህ ለውጦች ውጥረቱን ቢያረግቡም፣ በኋላ ላይ በ[[ኮሎኔል አለም ዘውድ]] የሚመራ የዘውዱ ተቆርቋሪ ቡድን የእንዳልካቸውን አስተዳደር ለመጥቀም በማሰብ ብዙ የ[[አየር ኃይል]] መኮንኖችን ለእስር ዳረገ። በዚህ ሁኔታ የተበሳጨውና ተከፋፍሎ የነበረው የጦር ሠራዊቱ ክፍል፣ ኮ/ል አለም ዘውድ ከሚመራው ቡድን በማፈንገጥ በአንድ ልብ አመጽ ጀመረ። ሻለቃና ከሻለቃ በታች የሆኑት እነዚህ መኮንኖች በተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ የአገሪቱ ሰራዊት ሶስት ሶስት ተወካዮች ወደ አዲስ አበባ እንዲልኩ በማድረግ፣እርስ በርሳቸው በመሰባሰብ፣ ደርግን መሰረቱ።
 
== የደርግ አመሰራረት ==