ከ«ደርግ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

3,846 bytes added ፣ ከ9 ዓመታት በፊት
no edit summary
የዘውዱ መንግስት ለዚህ መልስ ይሆናል ብሎ ያስበውን ብዙ ጥቃቅን ለውጦችን አድርጓል፤ ለምሳሌ አክሊሉ ሃብተወልድን አንስቶ [[እንዳልካቸው መኮንን]]ን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጓል፣ ለወታደሩ ልዩ ደመዎዝ ጭማሪ አድርጓል፣ ሊተገበር የነበር የትምህርት ስርዓት ማሻሻያ ለውጥን በተነሳበት ተቃውሞ ምክንያት አስቁሟል፣ የካቲት ወር ላይ እንዲሁ የ1947ቱን [[ሕገ መንግስት]] ለማሻሻል ሞክሯል። ምንም እንኳ እኒህ ለውጦች ውጥረቱን ቢያረግቡም፣ በኋላ ላይ በ[[ኮሎኔል አለም ዘውድ]] የሚመራ የዘውዱ ተቆርቋሪ ቡድን የእንዳልካቸውን አስተዳደር ለመጥቀም በማሰብ ብዙ የ[[አየር ኃይል]] መኮንኖችን ለእስር ዳረገ። በዚህ ሁኔታ የተበሳጨውና ተከፋፍሎ የነበረው የጦር ሠራዊቱ ክፍል፣ ኮ/ል አለም ዘውድ ከሚመራው ቡድን በማፈንገጥ በአንድ ልብ አመጽ ጀመረ። ሻለቃና ከሻለቃ በታች የሆኑት እነዚህ መኮንኖች በተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ የአገሪቱ ሰራዊት ሶስት ሶስት ተወካዮች ወደ አዲስ አበባ እንዲልኩ በማድረግ፣እርስ በርሳቸው በመሰባሰብ፣ ደርግን መሰረቱ።
 
== የደርግ አመሰራረት ==
== ድህረ አብዮት ==
[[ስዕል:መንግስቱ-ተፈሪ-አጥናፉ.gif|250px|thumb|right|የአብዮቱ ዋዜማ መሪዎች፣ [[ሻለቃ መንግስቱ ኃይለ ማርያም]]፣ ብ/ር ጀኔራል [[ተፈሪ በንቲ]]፣ ሊ/ት ኮሎኔል [[አጥናፉ አባተ]]]]
 
ኮ/ል አለም ዘውድ የዘውዱ ተቆርቋሪ እንደሆነ ከታመነበት በኋላ በኮ/ል አጥናፉ አባተ የሚመራ፣ ባብዛኛው ከ[[ሆለታ ጦር ማሰልጠኛ]] የተመረቀ ቡድንና ጥቂት [[የሐረር መኮንኖች ማስለጠኛ]] ምሩቆች ሁነው አክራሪ አብዮተኛ ቡድን መስርተው ከአለም ዘውድ ቡድን ተገንጥለው ወጡ። ይህ ቡድን በኮሚቴ በመዋቀር በአገሪቱ ከሚገኙ 42 የጦር ክፍሎች ሦስት ሦስት ወኪሎች ወደ አዲስ አበባ እንዲመጡ ካደረገ በኋላ ከሰኔ '66 ጀምሮ መደበኛ ስብስባ በማድረግ ''ደርግ''' እንዲቋቋም አደረገ። በአነጋገር ጥንካሬው፣ ውሳኔ ለመወሰን ባለምፍራቱና ባለማመንታቱ ታዋቂነት ያተረፈው [[መንግስቱ ኃይለማርያም]] [[ኢትዮጵያ ትቅደም]] የሚለውን መፈክር ካስተዋወቀ በኋላ በጣም ተቀባይነትን በማግኘቱ የዚሁ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሆኖ ተመረጠ። ኢትዮጵያ ትቅደም የሚለውን መፈክር ባስተዋወቀበት ንግግሩ ኮሚቴው ኢትዮጵያን ከመበታተን አደጋ ለማዳን የቆመ ኃይል አድርጎ በማቅረብ ለተዘበራረቀው አብዮት አቅጣጫ ከመስጠቱም በተጨማሪ የአገሪቱን አንድነት ለማስጠበቅ የሚችል ሃይል ይሄው ኮሚቴ እንደሆነ በማሳየት ለኮሚቴው የሃገር ጠባቂነትን አላማ ለማሰጠት ችሎ ነበር።
 
መንግስቱ፣ ምንም እንኳ በወታደሩ ዘንድ ተቀባይነት ቢያገኝም፣ በመላው ሃገሪቱ ዘንድ ሙሉ ተቀባይነትን ማግኘት እንደማይችል ስለተረዳ ለዚህ ተግባር እንዲረዳው ጄኔራል [[አማን አንዶም]]ን የስርዓቱ መሪ እንዲሆን በመጋበዝ የጊዜያዊው አስተዳደር ደርግ መሪ እንዲሆን አደረገ። ቀጥሎም ለዓፄ ኃይለሥላሴ 5 ጥያቄዎችን በማቅረብ ንጉሱ አምስቱንም ስለፈቀዱ የደርግ ሃይል በቅጽበት እንዲያድግ አደረገ።
 
በመቀጠል፣ በሃይል የጎለበተው ደርግ ጠቅላይ ሚንስትር እንዳልካቸው ከስልጣን እንዲነሱ አድርጎ [[ሚካኤል እምሩ]]ን ተካ። አማን አንዶም መከላከያ ሚንስትር ሆነው ከተሾሙ በኋላ እንዳልካቸውና የርሳቸው ደጋፊዎች እንዲታሰሩ ተደረገ። በዚህ መልኩ ቀስ ብሎ ይካሄድ የነበረው ለውጥ ፍጥነት ጨመረ። መንግስቱ፣ ንጉሱ እራሳቸውን በቀጥታ መጋፈጥ ስላልፈለገ ቀስ በቀስ የኃይላቻውን መዋቅር በማፈራረስ፣ የ[[ክብር ዘበኛ]]ን መሪ በማሳሰር፣ በኋላም የ[[ጆናታን ዲምብሊ]]ን [[የወሎ ረሃብ]] ቪዲዮ በቴሌቪዥን በማቅረብ ንጉሱ ተጠያቂ መሆናቸውን በማሳየት፣ ሙሉው ስራ ከተሰራ በኋላ ያለምንም ችግር ንጉሱን ከስልጣን ማስወገድ ቻለ።
 
=== የጊዚያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ ==
ንጉሱ ከስልጣን ከተነሱ በኋላ [[ጄኔራል አማን አንዶም]] የጊዚያዊ ወታደራዊ ደርግ ዋና ሊቀመንበር ሆኖ በመሾም፣ አዲሱ ስርዓት መስከረም፣ 1967 ተጀመረ። ደርግ በዚህ አኳሃን ስልጣን ላይ እንደወጣ አዲስ ረቆ የነብረውን [[ህገ መንግሥት]] እና የነበረውን [[ፓርላማ]] ወዲያው ሰረዘ።
 
 
 
 
=== አመሠራረት እና ዕድገት ===
13,558

edits