ከ«ደርግ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 3፦
 
== የአብዮቱ ዋዜማ==
[[የታኅሣሥ ግርግር]] ተብሎ በሚታወቀውና በ1953 ዓ.ም. የተካሄደው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ከከሸፈ በኋላ የ[[ቀዳማዊ ዓፄ ኃይለ ሥላሴ]] ዘውዳዊ መንግስት የተለያዩ ማሻሻያ ለውጦችን ለስርዓቱ አስተዋወቀ። አብዛኛዎቹ ማሻሻያዎች መፈንቅለ መንግስቱን እንዲደግፉ ለሚጠረጠሩ የጦርና የፖሊስ ሃይሎች የመሬት ስጦታ በማድረግ ላይ ያተኮረ ነበር። ስለሆነም የአገሪቱ መሰረታዊ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ሁኔታ በቋሚ ሁኔታ ሊሻሻል አልቻለም።
 
በ1958ዓ.ም. የባለ [[ርስት|ርስቱን]] መደብ ጉልበት ለመቀነስ በማሰብ የዘውዱ ሥርዓት አዲስ አይነት የመሬት [[ግብር]] ለማስተዋወቅ ሞከረ። ሆኖም [[የኢትዮጵያ ፓርላማ|ፓርላማው]] ሙሉ በሙሉ ውድቅ አደረገው። በምትኩ፣ በሚቀጥለው ዓመት የእርሻ ውጤቶች ግብር ለፓርላማ ቀርቦ ጸደቀ። ምንም እንኳ የጸደቀው ግብር መንግስት ካቀረበው በጣም የተለወጠ ቢሆንም፣ በባለርስቱ መደብ አመጽ ማስነሳቱ አልቀረም። በተለይ በ[[ጎጃም]] ባለርስቶች በተነሳ አመጽ ምክንያት የሁለት አመት ወታደራዊ ዘመቻ በጎጃም ተደርጎ አመጹን ለማሸነፍ ስላልተቻለ መንግስት ወታደሩን ከጎጃም በማውጣት ግብሩን ሙሉ በሙሉ መሰርዝ ግድ አለው። እንዲያውም ወደኋላ፣ እስከ 1932ዓ.ም. የነበር የግብር እዳ በሙሉ ተሰረዘ። የጎጃሙ ሽንፈት ሌሎች ለውጥን የሚቃወሙ ክፍሎች እንዲያምጹ ከማበረታቱም በላይ ስርዓቱን ለሌላ አጣብቂኝ ዳረገው።
 
ለውጥን እሚቃወሙ ኃይሎች በሚያምጹበት በዚያው ወቅት፣ በተቃራኒው ለውጥን የሚፈልጉ ተማሪዎች፣ ገበሬዎችና፣ የሰራተኞች ማህበራት ባንጻሩ የኑሮ ውድነትን፣ ጉቦንና፣ የመሬት ሥርዓቱን በመቃዎም ማደም ጀመሩ። ይህ የተወሳሰበ ሁኔታ በእድሜ እየገፉ የሄዱት ንጉሱ ፊታቸውን ወደ ውጭ ጉዳይ እንዲያዞሩና የአገሪቱን የውስጥ ጉዳይ በጠቅላይ ሚንስትራቸው [[አክሊሉ ሃብተወልድ]] ጫንቃ ላይ እንዲያስቀምጡ አደረጋቸው።
 
ሥርዓቱ በሁለት ተጻራሪ አጣብቂኞች ውስጥ ገብቶ ባለበት በዚህ ወቅት በተፈጠረ የርሃብ፣ የኑሮ ውድነት፣ ሙስናና አጠቃላይ ቅሬታ የ[[1966]]ቱ አብዮት እንዲፈነዳ ግድ ሆነ። አብዮቱን ሀ ብሎ የጀመረው የ[[ወታደር|ወታደሩ]] መደብ ሲሆን፣ ጥር፣1966 ዓ.ም. [[ነገሌ]]፣ [[ሲዳሞ]] ላይ ሰፍሮ የነበረው የ[[ምድር ጦር]] ሠራዊት አዛዥ መኮንኖቻቸውን ሲያግቱ ይጀምራል። ጉዳዩ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በሚኖሩ የሰራዊቱ ክፍሎች ድጋፍን በማግኘቱ በወታደሩ መደብ ከመዛመቱም ባሻገር ወደ ተቀረው ዜጋም በመዝለል በመጋባቱ በብዙ ከተማዎች አመጽ መነሳት ጀመረ።
 
የዘውዱ መንግስት ለዚህ መልስ ይሆናል ብሎ ያስበውን ብዙ ጥቃቅን ለውጦችን አድርጓል፤ ለምሳሌ አክሊሉ ሃብተወልድን አንስቶ [[እንዳልካቸው መኮንን]]ን ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጓል፣ ለወታደሩ ልዩ ደመዎዝ ጭማሪ አድርጓል፣ ሊተገበር የነበር የትምህርት ስርዓት ማሻሻያ ለውጥን በተነሳበት ተቃውሞ ምክንያት አስቁሟል፣ የካቲት ወር ላይ እንዲሁ የ1947ቱን [[ሕገ መንግስት]] ለማሻሻል ሞክሯል። ምንም እንኳ እኒህ ለውጦች ውጥረቱን ቢያረግቡም፣ በኋላ ላይ በ[[ኮሎኔል አለም ዘውድ]] የሚመራ የዘውዱ ተቆርቋሪ ቡድን የእንዳልካቸውን አስተዳደር ለመጥቀም በማሰብ ብዙ የ[[አየር ኃይል]] መኮንኖችን ለእስር ዳረገ። በዚህ ሁኔታ የተበሳጨውና ተከፋፍሎ የነበረው የጦር ሠራዊቱ ክፍል፣ ኮ/ል አለም ዘውድ ከሚመራው ቡድን በማፈንገጥ በአንድ ልብ አመጽ ጀመረ። ሻለቃና ከሻለቃ በታች የሆኑት እነዚህ መኮንኖች በተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ የአገሪቱ ሰራዊት ሶስት ሶስት ተወካዮች ወደ አዲስ አበባ እንዲልኩ በማድረግ፣እርስ በርሳቸው በመሰባሰብ፣ ደርግን መሰረቱ።
 
== ድህረ አብዮት ==
 
=== አመሠራረት እና ዕድገት ===
== የመንግስቱ አመራር ==