ከ«ግብረ ስጋ ግንኙነት» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
መስመር፡ 1፦
'''ግብረ ስጋ ግንኙነት''' ወይም '''ሩካቤ ስጋ''' ማለት በሴትና በወንድ መካከል ለስሜት እርካታ የሚደረግ ግንኙነት ወይም ፍቅር መሥራት ነው። ይህም ለመባዛት ወይም ለመዋለድ አስፈላጊ ከመሆኑ በላይ የወሲብን እርካታዊ ፍላጎት ለማሟላት ሊሆን ይችላል።
 
በ[[ሥነ ሕይወት]] ዘርፍ ሲታይ፣ ወሲብ፣ የእንስትን (ሴትን) እና የተባእትን ([[ወንድ]]ን) ዘር በማዋሃድ ወይንም በማዳቀል፣ የሕያው ፍጡራን ዓይነታዊ ሕልውናዝርያ (species)፣ ከአሮጌ ወደ አዲስ እየታደስ፡ በቅጥልጣይ ረገድ ለረዥም ጊዜ እንዲቆይ የሚያስችል፣ ተፈጥሮ የቸረችው ተፈጥሯዊ ተግባር ነው። በእያንዳንዱ የፍጡር አይነት ወንድና ሴት ፆታዎች ይገኛሉ። እነዚህ ፆታዎች በየራሳቸው ዘርን ማስተላልፍ የሚችሉብት ልዮ የማዳቀያ ህዋሶችን በሰውነታቸው ወስጥ ይሠራሉ ወይንም ያዘጋጃሉ። [[Image:Sperm-egg.jpg|frame|<big>የተባእት ተስለክላኪ ዘር ህዋስ፣ ከእንስቷ ፍሬ ዘር ህዋስ ጋር፣ በእንስቷ አካል ውስጥ ሲገናኙ:</big>]]እነዚህ ልዮ ህዋሳት 'ጋሜት' (gametes) በመባል ይታወቃሉ። እነዚህ ልዩ ህዋሳት በአካልቸው ተመሳሳይ (በተለይ isogametes በመባል የሚታወቁት) ሊሆኑ ቢችሉም፣ ነገር ግን በአብዛኛው ጊዜ ከወንድና ከሴት የሚገኙት የዘር ህዋሳት በቅርፃቸውም ሆነ በአኳኋናቸው ይለያያሉ። የወንዱ የዘር ህዋስ፣ ምጥን ያለና በትንሽ ይዘት ብዙ ዘራዊ ምልክቶችን ማጨቅ እንዲችል ሆኖ የተሠራ ሲሆን፣ ይህንንም ይዞ ረጅም ርቀት መጓዝ እንዲችል የፈሳሽ ውስጥ ተስለክላኪነት ባህርይ ወይንም ችሎታ አለው። የሴቷ ልዩ ህዋስ፣ ከወንዱ ህዋስ ጋር ሲስተያይ በአካሉ አንጋፋ ሲሆን፣ ይህ የሆነበት ምክንያት ተንቀሳቃሽ ሳይሆን የረጋ ከመሆኑም ጭምር፣ ከወንድ ዘር ከተገናኘ በኋላ በውስጡ ለሚፈጠረው ሽል አስፈላጊውን ንጥረ ነገር መያዝ ስላለበት ነው።
 
የአንድ ፍጡር ፆታ የሚታወቀው በሚፈጥረው የዘር ህዋሥ አይነት ነው። ተባእት ፍጡራን የተባእትን የዘር ህዋሥ (spermatozoa, or sperm) ሲፈጥሩ፣ እንሥት ፍጡራን የእንሥትን የዘር ህዋሥ (ova, or egg cells) ይፈጥራሉ።
የተወሰኑ የፍጡር አይነቶች፣ የተባእትንም የእንስትንም የዘር ህዋሥ ከአንድ ግላዊ አካል የሚያፈልቁ ሆነው ይገኛሉ። እነዚህ ፍናፍንት (hermaphroditic) በመባል ይታወቃሉ።
 
አብዛኛውን ግዜ የአንድ አይነታዊ ፍጡርዝርያ ተቃራኒ ፆታዎች፣ የተለያየ የአካል ቅርፅና የፀባይ ባህርይ ይታይባቸዋል። ይህ ልዩነት ሁለቱ ፆታዎች ያለባቸውን የእርባታ ኃላፊነትና የሚያስከትለውን አካላዊ ተፅእኖ ያንፀባርቃል።
 
==ወሲባዊ እርባታ==