ከ«ግብረ ስጋ ግንኙነት» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 10፦
==ወሲባዊ እርባታ==
[[Image:Sexual cycle.svg|thumb|200px|right|በወሲባዊ ዘዴ የሚራቡ ፍጡራን ህልውና፣ በህፕሎይድና በዳፕሎይድ ደረጃዎች ውስጥ ማለፍ አለበት ]]
ይህ ተግባር፣ ከላይ እንደተጠቀሰው፣ የእንስትና የተባእትን ዘር በማዋኃድ ወይንም በማዳቀል፣ የህያው ፍጡራን ዝርያ (Species)፣ ከአሮጌ ወደ አዲስ እየተታደስ፡ በቅጥልጣይ ረገድ ለረዥም ጊዜ እንዲቆይ የሚያስችል፣ ተፈጥሯዊ ተግባር ነው። በዘር ሀዋሣት ውህደት ወቅት ክሮሞሶም (Chromosomes) ከአንዱ ለጋሽ (ወላጅ) ወደሌላው ይተላለፋል። እያንዳንዱ ተሣታፊ ህዋሥ የለጋሾችን ግማሽ ክሮሞሶም ይይዛል። ግማሽ የአባት፣ ግማሽ የእናት ክሮሞሶሞች ተገናኛተው ይዋሃዳሉ ማለት ነው። ተወራሽ የዘር ምልክቶች፣ ዲ-አክሲ-ሪቦ-ኒውክሊክ አሲድ ወይንም ዲ-ኤን-ኤ (deoxyribonucleic acid (DNA)) በመባል በሚታወቀው፣ በክሮሞሶሞች ውስጥ የሚገኝ ንጥረ ነገር ውስጥ ሰፍረው ይገኛሉ። ይህ ውህደት ክግማሽ የአባት፣ ክግማሽ የእናት ክፍል የተስራ የክሮሞሶም ጥማድ ይፈጥራል። ክሮሞሶሞች በጥንድ ሆነው በሚገኙበት ጊዜ ዳይፕሎይድ (diploid) ይባላሉ። ክሮሞሶሞች በአሃዳዊ ህላዌ ግዜ ሃፕሎይድ (haploid) ይባላሉ። ዳይፕሎይድ የሃፕሎይድ ህዋስን (ጋሜት (gametes)) መፍጠር ይችላሉ። ይህ የሃፕሎይድ ጥንሰሳ ሂደት ሚዮሲስ (meiosis) በመባል ይታወቃል። ሚዮሲስ የሚባለው ሂደት የክሮሞሶማዊ ቅልቅል (chromosomal crossover) ሁኔታን ሊፈጥርም ይችላል። ይህ ሁኔታ መሳ በሆኑ ክሮሞሶምች መካከል የሚፈፀም ሲሆን፣ የክሮሞሶሙ ዲ-ኤን-ኤ ከባቢ ተቆርሶ ከሁለተኛው ክሮሞሶም ዲ-ኤን-ኤ ከባቢ ጋር ይዋሃዳል። ተራፊዎቹ ዲ-ኤን-ኤ እርስ በርሳቸው ባኳያቸው ይዋሃዳሉ። ውጤቱም በባህርይ ከበኩር ዳይፕሎይድ የተለየ አዲስ ዳይፕሎይድ መፍጠር ነው። ይህ የክሮሞሶም ቅልቅል ሂደት ከለጋሽ ወላጆች በተፈጥሮ ባህሪው የተለየ አዲስ አይነታዊ ፍጡርዝርያ (Species) ይከስታል።
 
በብዙ ፍጡራን የርቢ ሂደት ውስጥ የሀፕሎይድ ክስተት፣ ጋሜት በመፍጠር ላይ ብቻ ያተኮረ ነው። በዚህ ሁኔታ የሚገኙት ጋሜት እርስ በርሳቸው በመቀላቀል ዳይፕሎይድ መከሰት እንደሚችሉ ሆነው የተዘጋጁ ናቸው። እንዲሁም በሌሎች ፍጡራን ርቢ ጊዜ ጋሜት ራሳቸውን በመክፈል አዲስና ልዩ ልዩ የአካል ህዋሣትን መፍጠር ይችላሉ። እነዚህ በዚህ ሁኔታ የሚፈጠሩ የአካል ህዋሣት ሃፕሎይድ ክሮሞሶም ይኖሯቸዋል። በሁለቱም በኩል የሚገኙት ጋሜት በውጭ አካላቸው ተመሣሣይነት ያሳያሉ። ሆኖም ግን በአካላቸው የማይመሳሰሉ ጋሜት ይገኛሉ። በተለምዶ ተለቅ ያሉት ጋሜት የእንስት ህዋስ (ovum, or egg cell) ሲሆኑ፣ አነስ ያሉት ደግሞ የተባእት ህዋስ (spermatozoon, or sperm cell) ናቸው። በአካል መጠን ተልቅ ያለ ጋሜት የሚያመነጭ ግለፍጡር የእንስትነትን ፆታ ይይዛል፣ እንዲሁም አነስ ያለ ጋሜት የሚያመንጭ ግለፍጡር የተባእትን ፆታ ይይዛል። ሁለቱንም አይነት ጋሜት በአካሉ ውስጥ የሚያመነጭ ግለፍጡር ፍናፍንት (hermaphrodite) ይባላል። በአንዳንድ ሁኔታ hermaphrodite ራሳቸውን በራሳቸው በማዳቀል፣ ያላንዳች ወሲባዊ ጓደኛ አዲስ አካል (ፅንሥ) መፍጠር ይቸላሉ ።