ከ«ንግሥት ኤልሣቤጥ ዳግማዊት» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ «የንግሥት ኤልዛቤት ዳግማዊት 60ኛ ዓመት የአልማዝ የንግሥ በዓል አከባበር ተደርጓል ባለፈው እሑድ ...»
(No difference)

እትም በ10:32, 10 ጁን 2012

የንግሥት ኤልዛቤት ዳግማዊት 60ኛ ዓመት የአልማዝ የንግሥ በዓል አከባበር ተደርጓል

ባለፈው እሑድ ለንደን ውስጥ በቴምስ ወንዝ ላይ ከአንድ ሺሕ በላይ መርከቦችና ጀልባዎች የተሳተፉበት የንግሥት ኤልዛቤት ዳግማዊት 60ኛ ዓመት የአልማዝ የንግሥ በዓል አከባበር ተደርጓል፡፡


አሥራ አራት ድልድዮችን ያቋረጠው ይኼው የ12.1 ኪሎ ሜትር የቴምስ ወንዝ ላይ ጉዞ ንግሥቲቷን፣ የንጉሣውያን ቤተሰቦችንና ሌሎች ባለሥልጣናትን ያሳተፈ ሲሆን፣ በቴምስ ወንዝ ዳርቻዎች ላይ 1.2 ሚሊዮን ሰዎች በአካል ተገኝተው ተመልክተውታል፡፡

ይህ ክብረ በዓል በቢቢሲ፣ በስካይ ኒውስና በሌሎች ዓለም አቀፍ ቻናሎች በቀጥታ ከመተላለፉም በላይ፣ በጊነስ የዓለም ሪከርዶች መዝገብ ከፍተኛውን ሥፍራ መያዙ ተነግሮለታል፡፡ የእንግሊዝ ጦር ኃይል ጠቅላይ አዛዥ የሆኑት ንግሥት ኤልዛቤት የ86 ዓመት አዛውንት ናቸው፡፡