ከ«መቀሌ አሉላ አባ ነጋ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ «{{የቦታ መረጃ | ስም = መቀሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ | ሌላ_ስም = አሉላ አባ ነጋ | አገር ...»
 
No edit summary
መስመር፡ 18፦
መቀሌ አሉላ አባ ነጋ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በ[[ትግራይ ክልል]] ርዕሰ ከተማ ከ[[መቀሌ]] በአሥር ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ዘመናዊ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ነው።
 
አየር ማረፊያው በዘመናዊ መልክ የተገነባ እና የተደራጀ ሲሆን ከባሕር ወለል በ ፪ሺ ፪መቶ ፶፯ ሜትር ከፍታ ላይ ይገኛል። ባሁኑ ጊዜ አየር ማረፊያው አንድ ባለ ፫ሺ ፮፻ ሜትር ርዝመት በ፵፫ ሜትር ስፋት ያለው አስፋልት የለበሰ ማኮብኮቢያ ያለው ሲሆን እንደ ቦይንግ ፯መቶ ፶፯ አይነት አየር ዠበቦችን ማስተናገድ ይችላል። ዓለም አቀፍ በረራዎችን ለማከናወን የሚያስችሉት እንደ ጉምሩክ፣ ኢሚግሬሽን፣ የደህንነት ተቋማትና ኳራንቲን የመሳሰሉ መሰረተ ልማቶችን ያሟላ ነው።
 
[[የኢትዮጵያ አየር መንገድ]] [[ባሕር-ዳር]]ን እና [[መቀሌ]]ን ከ[[ካርቱም]] ጋር በማገናኘት [[ጥቅምት ፪]] ቀን [[2004|፳፻፬]] ዓ/ም ዓለም አቀፍ በረራ የጀመረ ሲሆን፣ የሁለቱን አገራት የንግድ፤ የቱሪዝምና የዲፕሎማሲ ግንኙነት ወደ ከፍተኛ ምዕራፍ ለማሸጋገር የላቀ ሚና እንደሚኖረው ይገመታል። የበረራ መስመሩ በሳምንት ለአራት ቀናት የሚከናወን ሲሆን፣ ሰሜን [[ሱዳን]]ን ከሰሜን የአገራችን ክፍል በቀጥታ የሚያገናኝ ነው። አየር መንገዱ ከ[[ሱዳን]] ለሚመጡ ጎብኝዎች የ[[አባይ ወንዝ]]ን ምንጭ፤ የ[[ጢስ እሳት ፏፏቴ]]ን፤ በ፯ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተገነባውን እና በ[[አፍሪቃ]] የመጀመሪያው መስጊድ እንደሆነ የሚነገርለትን [[አል ነጃሺ መስጊድ]] እና ሌሎችንም የሰሜን ኢትዮጵያ መስህቦዎችን ለመጎብኘት እንደሚያመቻች ይታመናል።