ከ«ጥቅማዊነት» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
r2.7.1) (ሎሌ መጨመር: war:Utilitarismo
No edit summary
መስመር፡ 1፦
'''ጥቅማዊነት''' ([[እንግሊዝኛ]]፦ Utilitarianism /ዩቲሊቴሪየኒዝም/) በ[[ፍልስፍና]] ስለ ድርጊት ትክክለኛነት የሚሰፍን ግብረ-ገባዊ ኅልዮ ነው። ከሁሉ የሚሻለው ድርጊት ለአብዛኛዎቹ ደስታ ወይም ጥቅም የሚያመጣው ያው ነው የሚለው ፍልስፍና ነው።
 
ጽንሰ ሃሣቡ በግሪኩበ[[ግሪክ (አገር)|ግሪኩ]] ፈላስፋ በ[[ኤጲቁሮስ]] ጽሑፍ ይገኛል። መርኁ ከጥንት ጀምሮ ቢታወቅም፣ በቅርቡ ዘመን ስለ ጥቅማዊነት በተለይ የጻፉት ፈላስፎች [[እንግሊዝ|እንግሊዞች]] [[ጄርሚ ቤንታም]] እና [[ጆን ስቱዋርት ሚል]] ነበሩ። ቤንታም እንደ ጻፈው የተሻለው ሥራ ለብዛቱ በጎ የሚሆነው ነው። በሱ ፍልስፍና አስተያየት ሰዎች ሁሉ ለ'2 ጌቶች' እነርሱም ለደስታና ለሀዘን ሲገዙ ይኖራሉ። ስለዚህ ለሰዎች በጎ የሆነ ሥራ ማለት ደስታን ማምጣትና ማብዛት እንደ ሆነ ገመተ። አንዱ ድርጊት ለጥቂቶች ደስ ቢያስን፣ ሁለተኛውም ለብዙዎች ደስ ቢያሰኝ፣ ሁለተኛው ይመረጣል ማለት ነው። ወይም እንደገና አንዱ ድርጊት ለ10 ሰዎች፣ ሁለተኛውም ለ5 ሰዎች ብቻ ደስታ ወይም ጥቅም ካመጣ፣ መጀመርያው የበለጠው ግብረገብ ነው ብሎአል። የቤንታም ደቀ መዝሙር ጆን ስቱዋርት ሚል 'ዩቲሊቴሪያኒዝም' በሚል መጽሐፍ ለፍልስፍናው ስሙን አወረሰ።
 
[[መደብ:ፍልስፍና]]