ከ«ምጽራይም» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
Robot-assisted disambiguation: ግሪክ - Changed link(s) to ግሪክ (ቋንቋ)
No edit summary
መስመር፡ 3፦
የ«''ሚጽራዪም''» ትርጉም በዕብራይስጥ ደግሞ [[ግብጽ]] (ምሥር) አገር ነው። እንዲሁም በ[[አረብኛ]] የአገሩ ስም '''مصر''' (ምጽር) ይባላል። ስሙ ዕጅግ የቆየ መሆኑ እርግጠኛ ነው። በ[[አካድኛ]] መዝገቦች የግብጽ ስም «ሙሱር»፣ «ሙስሪ»፣ በ[[ኡጋሪት]]ም ጽላቶች «ምስርም» ተብሏል።
 
አባ [[አውሳብዮስ]] በጻፉት ዜና መዋዕል ዘንድ፣ የድሮ ግብጻዊው ባለታሪክ [[ማኔጦን]] (3ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ.) ስለ ኋለኞቹ ግብጻውያን ሲጽፍ፣ ይኮሩበት የነበረው የታላቁ ጥንት ዘመን ከ[[ማየ አይህ]] አስቀድሞ እንዳለፈ፣ በኋላም በዚያው አገር ዳግመኛ ከሠፈረበት ከካም ልጅ ምጽራይም በውኑ እንደ ተወለዱ ጽፎ ነበር። ተመሳሳይ ታሪክ በ[[እስላም]] ጸሐፊዎች በግብጻዊው [[እብን አብድ ኤል-ሀከም]] እና በፋርሳውያን [[አል-ታባሪ]]ና [[ሙሐመድ ቈንዳሚር]] መጻሕፍት ሲገኝ፣ [[ፒራሚዶች]]፣ [[የጊዛ ታላቅ እስፊንክስ|እስፊንክስ]] ወዘተ. ሁሉ የተሠሩ ከጥፋት ውኃ በፊት በኖሩት ክፉ ዘሮች ሆኖ፣ ከዚያ በኋላ ግን አገሩ ለካም ተወላጅ ለምጽራይም (ማሣር ወይም መሥር) ተሠጠ ብለው ጻፉ። በነዚህም ደራስያን ዘንድ የመሥር ዕድሜ እስከ 700 መቶ አመት ድረስ ደረሰ።
 
በ[[ፊንቄ አፈ ታሪክ]] ደግሞ «[[ሚሶር]]» የሚባል ሰው የ[[ታዓውቶስ]] አባት ሲሆን የ[[ቢብሎስ]] ንጉሥ [[ክሮኖስ]] ግብጽን ለዚሁ ታዓውቶስ እንደ ሰጠ ይታመን ነበር።