ከ«ካም» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
r2.7.1) (ሎሌ መጨመር: ro:Ham
መስመር፡ 22፦
በ[[1490]] ዓ.ም. በጣልያናዊ መነኩሴ [[አኒዩስ ዴ ቪቴርቦ]] የታተመው «ሐሣዊ ቤሮሶስ» የተባለው ዜና መዋዕል ስለ ካም ሕይወት ብዙ ተጨማሪ መረጃ አለው። በዚህ በኩል፣ የኖህ ቤተሠብ ከመርከብ ወጥተው በ[[አርሜኒያ]] ገና ሲኖሩ፣ ካም ከጥፋት ውኃ በፊት የነበረውን ክፉ አስማት ተማረ፤ ደግሞ እሱ መጀመርያው [[ዞራስተር]] የተባለው ሆነ። ሌላ ስሙ «ካም ኤሴኑስ» (ካም መረኑ) እና [[ሳቱርን]] ([[ክሮኖስ]]) እንደ ነበር ይላል። ኖህ ከጥፋት ውሃ በኋላ ሌሎችን ሕጻናት ስለ ወለደ፣ ካም ኤሴኑስ በተለይ ቀናተኛ ሆነና አባቱን ጠላው። አንድ ቀን አባቱ ኖህ በድንኳኑ ሲሰከር በእራቁቱም ሲተኛ ካም አይቶ የሟርት ዘፈን በመዘምሩ በዚህ ምታት ጠንቅ ጊዜያዊ የወንድ አለመቻል በኖህ ላይ ደረሰበት፤ ኖህም ከዚያ ለጥቂት ወራት ልጅን መውለድ አልቻለም ነበር።
 
በኋላ አሕዛብ ወደ ርስቶቻቸው ተበትነው ካም ወደ አፍሪካ ሔዶ፣ ከጊዜ በኋላ በ[[ግብጽ]]ና በገዢው ''Oceanus'' (ውቅያኖስ) ላይ ወረደ፣ በዚያ አስማት በማስተማሩ የሰው ልጆች መልካም ጸባይ አወከ። አሕዛብ ከተበተኑ 112 አመታት በኋላ ካሜሴኑስ ከብዙ ሕዝብ ጋራ ከአፍሪካ በ[[ጣልያን]] ላይ ደረሰ፤ እዚያም መንግስቱን ይዞ ወንጄል አሰተማረ። ከ25 አመት በኋላ ግን [[ያኑስ]] በጣልያ ደርሶ ካሜሴኑስ ጥፋት በማስተምር አግኝቶት ይህንን ሁኔታ ለ3 ዓመት ከታገሠ በኋላ ያኑስ ካሜሴኑስን ከጣልያን አባረረው። ካሜሴኑስም ወደ [[ሲሲሊያ]]<ref>በሲሲሊያ ደሴት አሁን [[አቺሬያሌ]] በተባለው ከተማ ልማድ፣ ከተማው «ካሜሴና» ተብሎ በካሜሴኑስ (ካም) እራሱ እንደ ተመሠረተ የሚል ጥንታዊ ጽሑፍ ተቀርጾ ይገኛል። Brydone's Tour through Sicily & Malta, 1840, p. 73-74.</ref> እንደ ሸሸ ይጻፋል።
 
በዚህ ሰዓት፣ የካም እኅት የኖህም ሴት ልጅ [[ሬያ]] የ[[ሊብያ]] ንጉሥ [[ሃሞን]] ንግስት ስትሆን ሃሞን ግን ከሌላይቱ ሴት ከ[[አልማንጤያ]] ጋር ልጁን [[ዲዮኒስዮስ]]ን ወልዶ ሬያም በቅናት ተቆጥታ፣ ልጁን በ[[ኒሳ (አፈ ታሪክ)|ኒሳ]] ከተማ በሥውር እንዲያድግ ተላከ። (ይህም ታሪክ ከጥንታዊ ግሪክ ትውፊቶች ጋር ተመሳሳይነት አለው።) ሆኖም ሬያ በቅናቷ ተይዛ ከሃሞን ለቅቃ ወጥታ ወደ ወንድሟ ወደ ካሜሴኑስ በሲኪሊያ ሄደች። ካሜሴኑስ ሕጋዊ ሚስቱን ኖኤላን (በመርከብ ያመለጠችው የአፍሪካውያን ዘር እናት) ከዚህ በፊት ትቶ ነበር፤ አሁንም ካምና እህቱ ሬያ በሲኪሊያ ብዙም ታላላቅ አይነት ሰዎች ዘር ወለዱ። ካሜሴኑስና ሬያ ከ16 '[[ቲታኖች]]' ጋር ከዚያ የሃሞንን መንግሥት ሊብያን ወረሩ፤ ሃሞንንም ከሊቢያ ወደ [[ክሬታ]] ደሴት አባረሩት። ያንጊዜ ካሜሴኑስ ወይም ካም ለግዜው የሊቢያ ንጉሥ ሆነ፤ በዚያም ሬያ [[ዩፒተር ኦሲሪስ]]ን ወለደችለት። ነገር ግን የሃሞን ልጅ ዲዮኒስዮስ አድጎ ከኒሳ ደርሶ የአባቱንም ቂም በቅሎ ካምንና ሬያን ከሊቢያ አባረራቸው። ዲዮኒስዮስም ልጃቸውን ኦሲሪስን ማርኮት እንጀራ-አባቱ ሆነና እሱን የግብጽ ፈርዖን እንዲሆን አደረገው።
ከ «https://am.wikipedia.org/wiki/ካም» የተወሰደ