ከ«ሀዲስ ዓለማየሁ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

28 bytes added ፣ ከ8 ዓመታት በፊት
no edit summary
[[Image:Haddis_alemayehu.jpg‎|thumb|right]]ደራሲ ዶ/ር '''ሀዲስ ዓለማየሁ''' ከአባታቸው ከቄስ ዓለማየሁ ሰለሞን እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ደስታ ዓለሙ በ[[ደብረ ማርቆስ]] አውራጃ በጎዛመን ወረዳ በእንዳዶምበእንጾር ኪዳነ ምኅረት ቀበሌ በ[[ጥቅምት 7]] ቀን [[1902|፲፱፻፪]] ዓ.ም. ተወለዱ። ገና በጨቅላ እድሜያቸው በቤተ ክርስቲያን የሚሰጠውን ትምህርት በቤተሰባቸው አጠገብና ባባታቸው አገር ደብረኤልያስ ሄደው የግእዝ ትምሕርት ቤት ቅኔ ተቀኝተዋል። የቤተክርስቲያን ስርዐታትንና መንፈሳዊ ትምህርትን በጎጃም ገዳማት በደብረ ኤልያስ፣ በደብረ ወርቅና በዲማ ከቀሰሙ በኋላ ወደ በ[[18181918|፲፱፻፲፰]] ዓ.ም.[[አዲስ አበባ]] በመሄድ በ[[ስዊድን]] ሚሽነሪ ትምህርት ቤት በኋላም በራስ [[ተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት]] ትምህርታቸውን ተከታተሉ። ለትንሽ ግዜ በአስተማሪነት ሥራ ተሰማርተው እንዳገለገሉ የፋሽስት [[ጣሊያን]] ወረራ ተከሰተ።
 
የ[[ኢጣልያ]] ወረራ ሲከሰት ከ[[ልዑል ራስ እምሩ ኃይለ ሥላሴ]] ጦር ጋር በምዕራብ [[ኢትዮጵያ]] በአርበኝነት ሲዋጉ ቆይተው በመያዛቸው ጣሊያን ከልዑል ራስ እምሩ ጋር በግዞት ለሰባት ዓመት በ[[ፖንዞ ደሴት]]ና በ[[ሊፓሪ ደሴት]] ታስረው ቆይተዋል።
3,107

edits