ከ«ጋኔን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
መስመር፡ 25፦
 
===በአዲስ ኪዳን===
በ[[ወንጌሎች]] በተለይም በ[[ማርቆስ ወንጌል]] ዘንድ፣ [[ኢየሱስ]] በልዩ ልዩ ደዌ ወይም በሽታ የተሰቃዩትን ሰዎች እየፈወሰ፣ ጋኔን ወይም ርኩስ መንፈስ ካደረበት ሰው ጋኔኑን በቃሉ ያወጣል።
 
*''[[የማቴዎስ ወንጌል]]'' 9፡32 - ኢየሱስ ጋኔን ካደረበት ዲዳ ሰው ጋኔኑን አወጣና ዲዳው ተናገረ፤ የ[[ፈሪሳውያን]] [[አይሁድ]] ወገን ግን «በአጋንንት አለቃ አጋንንትን ያወጣል አሉ»።
*''ማቴዎስ'' 11፡18፣ ''[[የሉቃስ ወንጌል]]'' 7፡33 - ኢየሱስ ስለ [[ዮሐንስ መጥምቁ]] ሲያስተምር አንዳንድ ሰዎች ጋኔን እንደ ነበረበት ይሉ እንደ ነበር ይገልጻል።
*''ማቴዎስ'' 12፡22 - ኢየሱስ ጋኔን ካደረበት ዕውር ዲዳ ጋኔኑን አወጣና ሰውዬው ተፈወሰ። ሕዝቡ ተገርሞ ኢየሱስ የ[[ዳዊት]] ልጅ ([[መሢሕ]]) እንደ ነበር ገመተ። የፈሪሳውያን ወገን ግን ይህ በ[[ብዔል ዜቡል]] በአጋንንት አለቃ ነው አሉ።
*''ማቴዎስ'' 15፡22-28 - አንዲት [[ከነዓን (ጥንታዊ አገር)|ከነዓናዊ]] ሴት ኢየሱስን «የዳዊት ልጅ ሆይ» ስትለው ጋኔን ከሴት ልጅዋ እንዲያወጣ ለመነችው።
*''[[የማርቆስ ወንጌል]]'' 7፡25-30 - ከነዓናዊት ሴት «[[ግሪክ]]፣ ትውልድዋም [[ሲሮፊኒቃዊ]]ት» ይባላል።
*''ሉቃስ'' 4፡33 - ኢየሱስ በ[[ምኲራብ]] ሲያስተምር፣ አንድ ርኲስ ጋኔን መንፈስ ያደረበት ሰው ጮኸበት። ኢየሱስ ጋኔኑ ከዚህ ሰው እንዲወጣ አዘዘና ጋኔኑ ሰውዬውን በመካከላቸው ጥሎት ከእርሱ ወጣ።
*''ሉቃስ'' 4፡41 - ብዙ ጊዜ አጋንንትን ሲያወጣ፣ እንዲህ ይጮሁ ነበር፤ የኢየሱስ መታወቂያ [[ክርስቶስ]] (መሢሕ) መሆኑን ስላወቁ ነበር።
*''ሉቃስ'' 9፡37-42 - አንድ ሰው ኢየሱስ ጋኔን ከወንድ ልጁ እንዲያወጣ ለመነው። ይህ ጋኔን ልጁን ስይዘው ይጮህና አረፋም እያስደፈቀው ያንፈራግጠው ነበር።
*''ሉቃስ'' 11፡14-26 - ኢየሱስ ጋኔን ከዲዳ ሰው አወጣና አንዳንድ በብኤል ዜቡል ነው ሲሉ ገሰጻችው፤ እርስ በርስዋ የምትለያይ መንግሥት ትጠፋለች ሲላቸው። ከዚያ ርኩስ መንፈስ ከሰው በወጣ ጊዜ ዕረፍት እየፈለገ ውኃ በሌለበት ቦታ ማለፉን ያስተምራል።
 
==ሌሎች ምንጮች==