ከ«ዒዛና» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
r2.7.1) (ሎሌ መጨመር: lt:Ezana
Robot-assisted disambiguation: ሳባ - Changed link(s) to ሣባ (የአረቢያ ግዛት)
መስመር፡ 1፦
'''ዒዛና''' (በ[[ግሪክ (ቋንቋ)|ግሪክ]]፡ '''ኤይዛናስ''')፣ ንጉሥ (ወደ 4ኛው ክ/ዘ አጋማሽ ዓ.ም.)፣ ከ[[አክሱም]] ነገስታት ሁሉ ገናና የሆነ የመጀመሪያው ክርስትያን ንጉሥ ነበር። ምናልባት ለአባቱ ለንጉሥ [[ኢላ-አሚዳ]]፡ የበኩር ልጁ ሳይሆን አይቀርም። ስለ እናቱ ሥም የሚናገር [[ታዓማኒ]] የጽሑፍ መረጃ እስካሁን ድረስ አልተገኘም። ከሁለተኛ ደረጃ ምንጮች መሠረት ግን የእናቱ ሥም [[ሶፍያ]] ይባላል። ሁለቱ ወንድሞቹ [[ሣይዛና]] እና [[ኃደፋ]] በአስተዳደር እና በውትድርና ሥራዎች ይረዱት ነበር። በተለያዩ ጊዜያት ባደረጋቸው ተከታታይ የግዛት ማስፋፍያ ዘመቻዎች፡ ንጉሥ ዒዛና ግዛቱን በስሜን [[ቤጃ]]ዎች፣ [[ካሡ]]ና [[ኖባ]] በተባሉ የተከዘ ቀበሌዎች፣ በ[[አትባራ]] እና በ[[አባይ ወንዝ (ናይል)|አባይ]] ወንዞች ፣ በምስራቅ በኩል በ[[አግወዛት]]፣ በደቡብ [[ስራኔ]] በተባለ የአፋን ምድሮች ላይ ወረራ እንደፈጸመ በ[[ግዕዝ]]፣ በጥንታዊ [[ዐረብኛ]]፣ እና በ[[ግሪክ (ቋንቋ)|ግሪክ]] ተጽፈው በ[[አክሱም]] የተገኙ የጽሑፍ መረጃዎች ያመለክታሉ። የግዛት ማስፋፍያ ዘመቻዎቹ ቅደም ተከተል ግን እስካሁን አከራካሪ ናቸው። ንጉሥ ዒዛና ከሚጠቀሱለት የአስተዳደር ባሕርያት ውስጥ፤ የተቀናቃኞችን እና የአመፀኞችን ግዛቶች ካስገበረ በኋላ በምሕረትና በበጎ አስተዳደር ሥርዓት መተካቱ ፣ የአመፀኞችን ኃይል ለመስበር የሚያደርጋቸው የርስት ነቀላና የተለዋጭ ሠፈራ እርምጃዎች ተጠቃሽ ናቸው። የዙፋኑ ሥያሜም፦ ዒዛና የአክሱም፣ [[ሒምያር]]፣ [[ራይዳን]]፣ [[ሣባ (የአረቢያ ግዛት)|ሳባ]]፣ [[ሳልሄን]]፣ [[ሲያሞ]]፣ [[ቤጋ]] ([[ቤጃ]]) እና [[ካሡ]] ንጉሥ ነበር። የደቡብ ዓረብያ ግዛቶች ሥም በዙፋኑ ሥያሜ መካተታቸው ከንጉሣዊ ራዕይ ወይም ምኞት የመነጩ እንጂ በእርግጥም በግዛቱ የተጠቃለሉ የባሕር ማዶ አውራጃዎች ናቸው ለማለት የሚያበቃ በቂ መረጃ የለም። ከወርቅ፣ ከብር እና ከነሓስ በተቀረጹት ገንዘቦቹ ላይ «ዒዛና ዘሐለን፣ የአክሱሞች ንጉስ» የሚል ጽሑፍ ይነበባል።
 
በንጉሥ ዒዛና ዘመን፡ አክሱማውያን በዓለም-ዓቀፍ ንግድ ረገድ እንደ ዝሆን ጥርስ፣ ወርቅ፣ የዔሊ ክዳን፣ ቆዳ፣ ቅመማ ቅመም ወዘተ ወደ ውጭ ይልኩ እንደነበር፤ እንዲሁም ከወደ [[ሕንድ]] የሚመጡ ሽቀጦችን በመጨመር ከ[[ግሪኮች]]ና ከ[[ሮማዊያን]] ጋር የ[[አዱሊስ]] ወደብን በመጠቀም የንግድ ልውውጥ ያካሂዱ እንደነበር፣ በመዲናዋም የውጪ ዜጎችን ጨምሮ፣ ነጋዴዎች እና በልዩ ልዩ የሙያ መስኮች የተስማሩ በርካታ ነዋሪዎች ይኖሩባት እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ።