ከ«ነፋሳዊ ኤሌክትሪክ ማመንጫ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
መስመር፡ 1፦
'''ንፋሳዊ ኤሌክትሪክ ማመንጫ''' የ[[ንፋስ]]ን [[አቅም]] ወደ [[ኤሌክትሪክ]] አቅም የሚቀይር መሳሪያ ነው። ኤሌክትሪክ ማመንጫው አብዛኛውን ጊዜ ከ4 አበይት ክፍሎች ይዋቀራል። እኒህም [[#ዘዋሪ ላባ]]፣ [[ዳይናሞ#ጄኔሬተር ቆጥ]]፣ [[#መቆጣጠሪያ ስርዓት]] እና ዘዋሪውንና[[#የነፋሳዊ ዳይናሞውንኤሌክትሪክ ማመንጫ ሰገነት]] የሚሸከሙናቸው ዘንጎች ናቸው።
 
ዘዋሪው ላባ በንፋስ ጉልበት ሲሽከረክረ፣ እርሱ በተራው ዳይናሞውን (የ[[መግነጢስ]] እና ጥቅልል [[መዳብ]] ሽቦ ስርዓት) በመዘወር ኤሌክትሪክ እንዲመነጭ ያደርጋል። የመቆጣጠሪያ ስርዓቱ፣ የሚመነጨው ኤሌክትሪክ እንዳፈለገ እንዳይለዋወጥ፣ በተወሰነ መጠን እንዲረጋ የሚያደርግ የኮምፒዩተር ስርዓት ነው።
 
Line 22 ⟶ 21:
ከአራቱ፣ ሦስቱ በክብ ብረት ላይ በብሎን ይታሰራሉ። አራተኛው ላባ፣ ግልጋሎት ላይ የዋሉት ላባዎች ጉዳት ሲደርስባቸው ለመቀየሪያነት ያገልገላል። አራቱንም ላባ በአንድ ላይ መጠቀም ዋጋ የለውም።
 
== ጄኔሬተር ቆጥ ==
{{መዋቅር}}
የዘዋሪው ላባ ሲሽከረከር የሚፈጥረውን አቅም ወደ ኤሌክትሪክ አቅም ለመቀየር [[ጄኔሬተር]] ወይንም [[ዳይናሞ]] ያስፈልጋል። ጄኔረተሮች የሚሰሩት ከጥቅልል ሽቦ እና ከ[[መግነጢስ]] ሲሆን ለኤሌክትሪክ ማመንጫ የሚያስፈልግን ያክል ጄኔሬተር በ እጅ ለመስራት ከባድ ነው። ስለሆነም ለነፋስ ኤሌክትሪክ ማመንጫ የሚሆን ጄኔሬተር ወይም ከሱቅ መገዛት አለበት ወይንም ከተጣለ [[መሮጫ ማሽን]] ውስጥ በማውጣት፤ ወይንም ደግሞ ከተጣለ [[መኪና]] ውስጥ ኦልተርኔተሩን በማውጣት ለዚህ ጥቅም ማዋል ይቻላል።
 
ጄኔሬተሩ ክተገኘ በኋላ ከግራ በኩል በሚታየው ስዕል መሰረት በጄኔረተር ቆጡ ላይ በሚገባ ማሰር ግድ ይላል። ከጄኔረተሩ በተቃራኒ የቆጡ ጅራት በስዕሉ በሚታየው መልክ ይሰካል። የጅራቱ ተግባር የጄኔረተሩን ቆጥ በነፋስ ኃይል በማዞር ጄኔረተሩ ላይ የሚሰካው ዘዋሪ ላባ ምንጊዜም ወደተሻለ የንፋስ አቅጣጫ እንዲዞር ማድረግ ነው። ከቆጡ ስር የሰገነት ዘንጉ ይታያል። ዘንጉ በቆጡ ስር በሚበጅ ቀዳዳ በምግባት ቆጡን ሲደግፍ በዚያው መጠን ደግሞ ቆጡ እንደልቡ እንዲሽከረከር ያደርጋል። ውስጡ ክፍት ስለሆነ ከጄኔሬተሩ የሚመጡት ሽቦዎች በውስጡ ያልፋሉ።
 
== የነፋሳዊ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ሰገነት ==
ሰገነቱ ከመሬት ውስጥ በሲሚንቶ ይቀበርና ከመሃሉ ደግሞ በቋሊማ (መወጠሪያ ገመዶች) እንደ [[ድንኳን]] በችካል ይገተራል። የሰገነቱ ርዝመት ሲጨምር የሚያገኘውም ነፋስ ከፍ እያለ ስለሚሄድ ቁመቱ ከፍ እንዲል ፍላጎት አለ።
 
== መቆጣጠሪያ ስርዓት ==
በዚህ ማሽን የሚገኘው ኤለክትሪክ መጠን እንደ ነፋሱ ጉልበት ይወሰናል። ሆኖም ግን የኤሌክትሪክ እቃዎች የኤሌክትሪክ መጠን መቀያየርን አይወዱም፣ ስለሆነም የጄኔሬተሩ የሚመነጨው ኤሌክትሪክ ከቁጥጥር ውጭ እንዳይሆን መጠኑን መቆጣጠር ግድ ይላል። ለዚህ ተግባር [[ዳዮድ]] እና መሰል ኤሌክትሪክ አካላትን መጠቀም ይቻላል።
 
== ተጨማሪ ንባቦች/ ቪዲዮዎች {{en}} ==
* [http://makeprojects.com/Project/Make-a-Wind-Generator/9/1 በጣም ዝርዝር የሆነ ገለጻ - ከ20 በላይ ደረጃዎች]
* [http://www.wonderhowto.com/how-to-make-wind-powered-generator-with-make-magazine-272175/ አሰራር ቪድዮ]
* [http://www.builditsolar.com/Projects/Wind/wind.htm በጥልቀት ለማንበብ ለሚፈልጉ ]
 
[[መደብ: ኤሌክትሪክ]]