ከ«አሙን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
Robot-assisted disambiguation: ኩሽ - Changed link(s) to የኩሽ መንግሥት
መስመር፡ 1፦
[[ስዕል:Amun5.jpg|thumb|200px|አሙን]]
 
'''አሙን''' (ደግሞ '''አመን፣ አሞን፣ ሃሞን''') በጥንታዊ [[ግብጽ]] [[አረመኔ]] እምነት ዘንድ ከነበሩት ዋና አማልክት (ጣኦታት) አንዱ ነበር። ከዚህ በላይ በጥንታዊ [[ሊቢያ]]፣ [[የኩሽ መንግሥት|ኩሽ]] እና [[ግሪክ (አገር)|ግሪክ]] አገሮች አረመኔ እምነቶች ከፍተኛ ሚና ያጫወት ነበር።
 
በግብጻውያን ሃይማኖት፣ አሙን ያልተወለደ ያልተፈጠረ ፈጣሪ መሆኑ ይታመን ነበር። ከ1550 ዓክልበ. የገዙት ፈርዖኖች በተለይ ያከብሩት ነበር። በጊዜ ላይ፣ የአሙን እና የ[[ፀሐይ]] ጣኦት [[ራ]] መታወቂያዎች አንድ ሆነው ስያሜው «'''አሙን-ራ'''» (ወይም «'''አሙን-ሬ'''») ይባል ጀመር። በ1360 ዓክልበ. ያህል ግን ፈርዖኑ [[4 አመንሆተፕ]] የራሱን ስም ወደ «አከናተን» ቀይሮ የአሙን አምልኮት ከለከለው፤ በፈንታውም የ[[አተን]] እምነት እንዳቆመ ይታወቃል። አከናተን በ1345 ዓክልበ. ግድም በሞተበት ወቅት፣ የአሙን-ራ ቄሳውንት ተነሥተው ሃይማኖታቸውን መለሡ፤ ስለዚህ የአከናተንም ልጅና ተከታይ ቱታንካተን ስሙን ወደ [[ቱታንካመን]] ሊቀይር ተገደደ።