ከ«ላፕላስ ሽግግር» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
r2.5.2) (ሎሌ ማስተካከል: th:การแปลงลาปลาส
r2.7.2) (ሎሌ መጨመር: ml:ലാപ്ലേസ് പരിവർത്തനം; cosmetic changes
መስመር፡ 1፦
በሒሳብ ጥናት ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ ስራ ላይ የሚውል የ[[መደመራዊ ሽግግር]] ቢኖር ይሄው [[ላፕላስ ሽግግር]] (Laplace Transform) የሚባለው ነው። ይህ ሽግግር በ[[ፊዚክስ]]፣[[ሒሳብ]]፣ በ[[ምህንድስና]]ና በ[[እድል ጥናት]] የዕውቀት ዘርፎች በከፍተኛ ስራ ላይ ይውላል። [[ሎጋሪዝም]] ማባዛትን ወደ መደመር እንደሚቀይርና ማባዛትን እንደሚያቃልል ሁሉ የላፕላስት ትራንስፎርም የካልኩለስን [[ሥነ ለውጥ]]ና [[ሥነ ማጎር]] ወደ ማባዛትና ማካፈል በማሻገር የካልኩለስን ተግባር ያቃልላል።
 
የላፕላስ ሽግግር ከ[[የፎሪየር ሽግግር|ፎሪየር ሽግግር]] ጋር ተዛማጅ ቢሆንም ቅሉ [[የፎሪየር ሽግግር]] ፈንክሽኖችን ወይም መልእክትን ወደ መስረታዊ የርግብግብ ክፍላቸው ሲበትናቸው የ[[ላፕላስ ሽግግር]] ግን ወደ መሰረታዊ [[ሂሳባዊ|ቅርጻቸው]] ይበትናቸዋል። ሁለቱም ግን የ[[ለውጥ እኩልዮሽ]]ን (ዲፈረንሺያል ኢኮዥን) ጥያቄወችን ለመፍታት የሚጠቅሙ ሂሳባዊ መሳሪያወች ናቸው። የላፕላስ ሽግግር በ[[ፊዚክስ]]ና በ [[ምህንድስና]] ከፍተኛ ጥቅም ያላቸው [[ጊዜ-የማይቀይራቸው ቀጥተኛ ]] (ሊኒያር ታይም ኢንቫሪያንት) ሥርዓቶችን ለመፍታት ሲሆን ይህ ጉዳይ የ[[ኤሌክትሪክ ምህንድስና]]ን፣ [[ብርሃን|ብርሃናዊ መሳሪያወች]] ምህንድስናን ሌሎች ተነቀሳቃሽ እቃወችን በቀላሉ ለመተለም ይረዳል። በዚህ የትንታኔ (analysis) ሥርዓት በጊዜ ግዛት ውስጥ ተቀምጠው ያሉ ጥያቄወችን ወደ [[ድግግሞሽ]] ግዛት ጣይቄዎች በማሻገር የሚደረገውን የስሌት ሂደት መቀነስ ነው።
 
<math>x(t) -->[system] --> y(t)</math> ... በጊዜ ውስጥ ያለ ስርዓት ሲሆን
 
<math> x(f) -->[system] -- > y(f)</math>.... በድግግሞሽ ግዛት ያለ ሥርዓት
 
የላፕላስ ሽግግር ምልክት ይሄን ይመስላል <math>\displaystyle\mathcal{L} \left\{f(t)\right\}</math> ። [[ቀጥተኛ ኦፕሬተር]] ሲሆን f(t)ን (t ≥ 0) ወደ F(s) (s እንግዲህ ድግግሞሽ [[ያቅጣጫ ቁጥር]] ነው ) ይቀይራል።
 
== ታሪክ ==
የላፕላስ ሽግግር በእውቁ የሒሳብና ከዋክብት ሊቅ [[ፒየ-ስሞን ላፕላስ ]] ስም የተሰየመ ሲሆን፣ ይሄው አጥኝ የሽግግሩን ግኝት የተጠቀመበት የ[[ዕድል]] ጥናቱን በቀላሉ ለማካሄድ ነበር። ከላፕላስ በፊት እርግጥ ነው [[ኦይለር]] የሚከተለውን አይነት [[ሥነ ማጎር]](ኢንቴግራል) አጥንቷል፦
:<math> z = \int X(x) e^{ax}\, dx\text{ and }z = \int X(x) x^A \, dx,</math>
ይህንም ያጠናው የአንድ አንድ [[ለውጥ እኩልዮሽ|ለውጥ እኩልዮሾችን]] መፍትሔ ለማግኘት ነበር፤ ነገር ግን ነግሩን ጠለቅ ብሎ የማየት ዝንባሌ አላሳየም። [[ዮሴፍ ሉዊ ላግራንግ]] የተሰኘው የፈረንሳይ የሂሳብ ሊቅም በበኩሉ የ[[ኦይለር]] አድናቂ እንደሞሆኑ መጠን የ[[እድል ችፍገት]]ን (probability density) ለማስላት ተመሳሳይ ፎርሙላ ተጠቅሟል፦
 
:<math> \int X(x) e^{- a x } a^x\, dx,</math>
 
ይህ ስሌት አሁን ካለንበት የላፕላስ ሽግግር ቀመር ጋር ተመሳሳይ ቢሆንም ቅሉ ያሁን እውቀት አካል እንጂ ሙሉ በሙሉ የላፕላስ ሽግግርን እንደማይወክል ስምምነት ላይ ተደርሷል። [[ላፕላስ]] በ1782አካባቢ ከላይ የተጠቀሰውን የ[[ኦይለርን]] ቀመር ለ[[ለውጥ እኩልዮሽ]] መፍትሔነት ቢመረምርም ቅሉ በ1785 በጣም ወሳኝ ርምጃ ወስደ። ይሄውም ከላይ የተጻፉትን ሥነ-ማጎሮች እንደ የ[[ዲፈረንሻል ጥያቄ]] ከማየት ይልቅ እራሳቸውን የቻሉ የፈንክሽን አሻጋሪወች መሆናቸውን ተገነዘበ። ለዚህም ስራው እንዲረዳው ይህን የመሰለ የማጎር ቀመር መጠቀም ጀመረ፦
:<math> \int x^s \phi (s)\, dx,</math>
አንዳንድ የሂሳብ ታሪክ አጥኘወች ይህን ፈንክሽን የዘመናዊው ላፕላስ ሽግግር [[ኅልዮት]] አካል አድርገው ያዩታል። <ref>{{harvnb|Lagrange|1773}}</ref><ref>{{harvnb|Grattan-Guinness| 1997|p=260}}</ref>
 
ተግባሩም አጠቃላይ የ[[ልዩነት እኩልዮሽ|ልዩነት እኩልዮሾችን]] ከከባድ ወደ ቀላል በማሻገር ምፍትሔያቸውን በተሻገረው ቅርጽ መፈለግ ነበር። ቀጥሎም አሁን የሚታወቀውን የላፕላስ ሽግግር በመመርመር ጥልቅ የሆነ እምቅ ጥቅሙን ለመገንዘብ ቻለ።<ref>{{harvnb|Grattan-Guinness|1997|pp=261&ndash;262261–262}}</ref> ላፕላስ የ[[ዮሴፍ ፎሪየር]]ን የሙቀት ሥርፀት ጥናትና የ[[ፎሪየር ዝርዝር]] መፍትሔውን ውሱን ኃይል በመተቸት በአዲሱ ቀመሩ ፎርየር ከፈታቸው ጥያቄወች የሰፉ ጥያቄወችን መልስ ለማግኘት ቻለ። <ref>{{harvnb|Grattan-Guinness|1997|pp=262&ndash;266262–266}}</ref>
 
== የላፕላስ ሽግግር ደንበኛ ትርጓሜ ==
መስመር፡ 33፦
 
 
=== ሁለት ጎን ላፕላስ ሽግግር ===
ላፕላስ ሽግግር ሲባል አብላጫውን ጊዜ ትርጓሜው አንድ ጎን ላፕላስ ሽግግር ማለት ነው (0 እና ከ0 በላይ) ። ነገር ግን የላፕላስ ሽግግር ሁሎንም የውን ቁጥሮች እንዲያሳትፍ ሆኖ ሊተረጎም ይችላል፣ ማለት የማጎሪያው መነሻና መድረሻ ከነጌቲቭ [[አዕላፍ]] እስከ ፖዚቲቭ አዕላፍ ማለት ነው። ሁለት ጎን የላፕላስ ሽግግር እንዲህ ይቀመራል፡
 
: <math>F(s) = \mathcal{L}\left\{f(t)\right\} =\int_{-\infty}^{\infty} e^{-st} f(t)\,dt.</math>
 
=== የላፕላስ ሽግግር ግልብጥ ===
 
[[የላፕላስ ሽግግር ግልብጥ]] በእንዲህ መልኩ በ[[አቅጣጫ ቁጥር]] ሥነ ማጎር ይጻፋል፡
መስመር፡ 46፦
እዚህ ላይ <math>\gamma</math> የውኑ ቁጥር ነው።
 
== የሽግግሩ ሥነ ማጎር ውሱን የሚሆንበት አካባቢ ==
''ƒ'' በየቦታው መታጎር የሚችል [[ከሆነ]] የ''ƒ'' ላፕላስ ሽግግር ''F''(''s'') ውሱን ነው የሚባለው የሚከተለው [[ጥገት]]
 
መስመር፡ 57፦
ኅልው ከሆነ የዚያ ፈንክሽን ላፕላስ ሽግግር [[ውሱን ፈንክሽን|ውሱን]] ነው፣ ስለሆነም አለ (ኅልው ነው)።
 
== የሽግግሩ ፀባዮችኛ እርጉጦች ==
የላፕላስ ሽግግር ፀባዮች ሊኒያር [[የእንቅስቃሴ]] ስርዓቶችን ተንትኖ ለመረዳት የሚያስችሉ ብዙ ጥሩ ጸባዮች አሉት። በተለይ ዋናው ለዚህ ጉዳይ የሚጠቅመው ፀባዩ [[ሥነ ለውጥ]]ን ወደ [[ማባዛት]] እና [[ሥነ ማጎር]]ን ወደ[[ማካፈል]] በመቀየር ሂሳብን ማቃለሉ ነው። ይህ እንግዲህ [[ሎጋሪዝም]] ማባዛትን ወደ ሎጋሪዝም መደመር እና ማካፈልን ወደ ሎጋሪዝም መቀነስ እንደሚቀይረው አይነት ባህርይ ነው። ስለሆነም የላፕላስ ሽግግር የ[[ለውጥ እኩልዮሽ]]ና የ[[ማጎር እኩልዮሽ]]ን ወደ [[ፖሊኖሚያል]] እኩልዮሽ በመቀየር ስራን ከማቀላጠፍ በላይ እጅግ ያቃልላል። በዚህ ወቅት በጊዜ t ግዛት ውስጥ የነበሩት እኩልዮሾች ወደ s ግዛት ስለሚሻገሩ፣ የተገኘውን የላፕላስ ሽግግር መፍትሔ ወደ ጊዜ ግዛት እንደገና መቀየር ግድ ይላል። ይሔውም የሚከናወነው በ [[#የላፕላስ ሽግግር ግልብጥ|መገልበጥ]] ነው።
 
መስመር፡ 65፦
: <math> g(t) = \mathcal{L}^{-1} \{ G(s) \} </math>
 
ይህን ልብ በማለት፣ የላፕላስ ሽግግር ዋና ዋና ጠባዮች ከታች ይቀርባሉ :<ref>{{harv|Korn|Korn|1967|p=226&ndash;227226–227}}</ref>
 
{| class="wikitable"
መስመር፡ 153፦
 
== በጊዜ ውስጥ ያለ የኤሌክትሪክ ኡደት የs-ግዛት ተመጣጣኙና እግዶሹ ==
የላፕላስ ሽግግር ብዙውን ጊዜ በኤሌክትሪክ ኡደት (ሰርኪዩት) ትንታኔ ላይ ተጠቃሚነትን ያገኛል። አብዛኛውን ጊዜ የተሰጠን [[የኤሌክትሪክ ዑደት| ዑደት]] ወደ s-ግዛት ተመጣጣኙ ማሻገር ቀላል ነው። የዑደቱ አባላት በቀላሉ ወደ ተመጣጣኝ [[እግዶሽ|እግዶሻቸው]] (ኢምፔዳንስ) ይቀየራል፣ ይኼውም [[ፌዘር]] እንደሚገኝበት ስሌት ነው እንጅ ልዩ አይደለም። የሚከተለው ምስል ይን ተግባር ባጭሩ ያሳያል {{en}}፦
 
: [[Fileስዕል:S-Domain circuit equivalency.svg]]
 
እዚህ ላይ [[ተቃዋሚ]](ሬዚዝስተር) በጊዜም ሆነ በኤስ-ግዛት አንድ አይነት ዋጋ አለው። የኤሌክትሪክ ምንጮች በዚህ ትንታኔ ውስጥ እንዳይወጡ የሚሆኑት ትንታኔ በሚጀመርበት ወቅት ዋጋ ካላቸው ነው። ለምሳሌ [[አቃቤ(ኤሌክትሪክ)|አቃቤው]] (ካፓሲተሩ) ሲጀመር ቮልቴጅ ካለው ፣ ወይንም [[ቃቤ (ኤሌክትሪክ)|ቃቤው]] (ኢንደክተሩ) በውስጡ የኤሌክትሪክ ጅረት ካለው፣ በ s-ግዛት ሆነው ያሉት ምንጮች በተሻጋሪው ዑደት ውስጥ መግባት ግድ ይላል።
 
 
መስመር፡ 166፦
[[መደብ:ኤሌክትሪካል ኢንጂኔሪንግ]]
[[መደብ:አልጀብራ]]
[[መደብ: ካልኩለስ]]
 
[[ar:تحويل لابلاس]]
መስመር፡ 192፦
[[ko:라플라스 변환]]
[[lt:Laplaso transformacija]]
[[ml:ലാപ്ലേസ് പരിവർത്തനം]]
[[nl:Laplacetransformatie]]
[[nn:Laplace-transformasjon]]