ከ«አሙን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 7፦
በ[[ኩሽ መንግሥት]]፣ በ[[ኖባ]] እና በ[[መርዌ]] አሙን «'''አማኔ'''» ተብሎ በተለይ ይወደድ ነበር። የአማኔ ቄሳውንት መንግሥትን በሙሉ ይቆጣጥሩ ነበር፤ ነገሥታትን መረጡ፣ ጦርነትንም አዋጁ። [[ዲዮዶሮስ ሲኩሉስ]] እንደሚለን እንኳን የአማኔ ቄሳውንት ንጉሥ ራሱን እንዲገድል ሊያዝዙ ይችሉ ነበር።
 
በሊቢያ የአሙን መቅደስ በበረሃ ውስጥ በ[[ሲዋ ኩሬ]] ይገኝ ነበር። ግሪኮቹም «'''[[ዚውስ]] ሃሞን'''» ሲሉት ወዲህወደ ሊቢያ ተጒዘው በየጊዜ ያማክሩት ነበር። የአሞን መቅደሶች ደግሞ በግሪክ አገር ሠሩ። ዲዮዲሮስ የሊቢያ [[አፈ ታሪክ]] ሲተርክልን፣ ሃሞን በ[[አፍሪካ]] (በ[[ኒሳ (አፈ ታሪክ)|ኒሳ]] ደሴት በ[[ትሪቶኒስ ሀይቅ|ትሪቶን ወንዝ]]) የገዛ ንጉሥ ነበረ፤ ሚስቱም [[ሬያ]] ነበረች። የሬያ ወንድም [[ክሮኖስ]] ግን ከ[[ቲታኖች]] ጋራ ወርሮ ሊቢያንም ሬያንም ከሃሞን እጅ ያዘ። ከዚህ በኋላ የሃሞን ልጅ [[ባኩስ]] ወይም [[ዲዮኒሶስ]] ክሮኖስን አሸነፈው፤ የክሮኖስና የሬያንም ልጅ [[ዩፒተር ኦሊምፑስ]]ን ማርኮ እርሱን የግብጽ አገረ ገዥ አደረገው።
 
ጣልያናዊ መኖኩሴ [[አኒዩስ ዴ ቪቴርቦ]] ባሳተመው ዜና መዋዕል ዘንድ ([[1490]] ዓ.ም. የታተመ)፣ ሃሞን የሊቢያ ንጉሥ የ[[ትሪቶን]] ልጅና ተከታይ ነበረ። የ[[ካም|ካሜሴኑስ]] (ካም) እኅት ሬያን አገባ። ሬያም በሥውር የሃሞንን ዲቃላ ሕጻን ልጅ ዲዮኒስዮስን ከቁባቱ ከ[[አልማንጤያ]] ወስዳ ወደ ኒሳ በ[[አረቢያ]] እንዲታደግ ላከችው። ስለዚህ ነገር ሃሞንና ሬያ ለረጅም ጊዜ ብዙ ተጣሉ። በመጨረሻ ሬያ ወደ ወንድምዋ ወደ ካሜሴኑስ በ[[ሲኪልያ]] ሸሽታ እርሱ አገባትና ከቲታኖቹ ጋራ ሊቢያን ወረሩ፤ ሃሞንንም ወደ [[ክሬታ]] ደሴት አባረረው። ካሜሴኑስና እህቱ ሬያም ልጃቸውን ''ዩፒተር ኦሲሪስ''ን ወለዱ። በኋላ ግን የሃሞን ልጅ ዲዮኒስዮስ ከኒሳ ተመልሶ ካሜሴኑስን አሸነፈው። ዲዮኒስዮስም የካሜሴኑስና የሬያን ልጅ ''ዩፒተር ኦሲሪስ''ን ማርኮ የግብጽ ንጉሥ እንዲሆን አደረገው። በዚህ ዜና መዋዕል አቆጣጠር ሃሞን በሊብያ የነገሠ ምናልባት ከ2315 እስከ 2287 ዓክልበ. ግድም ነበር።