ከ«አሙን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 3፦
'''አሙን''' (ደግሞ '''አመን፣ አሞን፣ ሃሞን''') በጥንታዊ [[ግብጽ]] [[አረመኔ]] እምነት ዘንድ ከነበሩት ዋና አማልክት (ጣኦታት) አንዱ ነበር። ከዚህ በላይ በጥንታዊ [[ሊቢያ]]፣ [[ኩሽ]] እና [[ግሪክ (አገር)|ግሪክ]] አገሮች አረመኔ እምነቶች ከፍተኛ ሚና ያጫወት ነበር።
 
በግብጻውያን ሃይማኖት፣ አሙን ያልተወለደ ያልተፈጠረ ፈጣሪ መሆኑ ይታመን ነበር። ከ1550 ዓክልበ. የገዙት ፈርዖኖች በተለይ ያከብሩት ነበር። በጊዜ ላይ፣ የአሙን እና የ[[ፀሐይ]] ጣኦት [[ራ]] መታወቂያዎች አንድ ሆነው ስያሜው «'''አሙን-ራ'''» (ወይም «'''አሙን-ሬ'''») ይባል ጀመር። በ1360 ዓክልበ. ያህል ግን ፈርዖኑ [[4 አመንሆተፕ]] የራሱን ስም ወደ «አከናተን» ቀይሮ የአሙን አምልኮት ከለከለው፤ በፈንታውም የ[[አተን]] እምነት እንዳቆመ ይታወቃል። አከናተን በ1345 ዓክልበ. ግድም በሞተበት ወቅት፣ የአሙን-ራ ቄሳውንት ተነሥተው ሃይማኖታቸውን መለሡ፤ ስለዚህ የአከናተንም ልጅና ተከታይ ቱታንካተን ስሙን ወደ [[ቱታንካመን]] ሊቀይር ተገደደ።
 
በ[[ኩሽ መንግሥት]]፣ በ[[ኖባ]] እና በ[[መርዌ]] አሙን «'''አማኔ'''» ተብሎ በተለይ ይወደድ ነበር። የአማኔ ቄሳውንት መንግሥትን በሙሉ ይቆጣጥሩ ነበር፤ ነገሥታትን መረጡ፣ ጦርነትንም አዋጁ። [[ዲዮዶሮስ ሲኩሉስ]] እንደሚለን እንኳን የአማኔ ቄሳውንት ንጉሥ ራሱን እንዲገድል ሊያዝዙ ይችሉ ነበር።