ከ«አሙን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
sp
መስመር፡ 5፦
በግብጻውያን ሃይማኖት፣ አሙን ያልተወለደ ያልተፈጠረ ፈጣሪ መሆኑ ይታመን ነበር። ከ1550 ዓክልበ. የገዙት ፈርዖኖች በተለይ ያከብሩት ነበር። በጊዜ ላይ፣ የአሙን እና የ[[ፀሐይ]] ጣኦት [[ራ]] መታወቂያዎች አንድ ሆነው ስያሜው «አሙን-ራ» ይባል ጀመር። በ1360 ዓክልበ. ያህል ግን ፈርዖኑ [[4 አመንሆተፕ]] የራሱን ስም ወደ «አከናተን» ቀይሮ የአሙን አምልኮት ከለከለው፤ በፈንታውም የ[[አተን]] እምነት እንዳቆመ ይታወቃል። አከናተን በ1345 ዓክልበ. ግድም በሞተበት ወቅት፣ የአሙን-ራ ቄሳውንት ተነሥተው ሃይማኖታቸውን መለሡ፤ ስለዚህ የአከናተንም ልጅና ተከታይ ቱታንካተን ስሙን ወደ [[ቱታንካመን]] ሊቀይር ተገደደ።
 
በ[[ኩሽ መንግሥት]]፣ በ[[ኖባ]] እና በ[[መርዌ]] አሙን «አማኔ» ተብሎ በተለይ ይወድድይወደድ ነበር። የአማኔ ቄሳውንት መንግሥትን በሙሉ ይቆጣጥሩ ነበር፤ ነገሥታትን መረጡ፣ ጦርነትንም አዋጁ። [[ዲዮዶሮስ ሲኩሉስ]] እንደሚለን እንኳን የአማኔ ቄሳውንት ንጉሥ ራሱን እንዲገድል ሊያዝዙ ይችሉ ነበር።
 
በሊቢያ የአሙን መቅደስ በበረሃ ውስጥ በ[[ሲዋ ኩሬ]] ይገኝ ነበር። ግሪኮቹም ወዲህ ተጒዘው በየጊዜ ያማክሩት ነበር። የአሞን መቅደሶች ደግሞ በግሪክ አገር ሠሩ። ዲዮዲሮስ የሊቢያ [[አፈ ታሪክ]] ሲተርክልን፣ ሃሞን በ[[አፍሪካ]] (በ[[ኒሳ]] ደሴት በ[[ትሪቶን]] ወንዝ) የገዛ ንጉሥ ነበረ፤ ሚስቱም [[ሬያ]] ነበረች። የሬያ ወንድም [[ክሮኖስ]] ግን ከ[[ቲታኖች]] ጋራ ወርሮ ሊቢያንም ሬያንም ከሃሞን እጅ ያዘ። ከዚህ በኋላ የሃሞን ልጅ [[ባኩስ]] ወይም [[ዲዮኒሶስ]] ክሮኖስን አሸነፈው፤ የክሮኖስና የሬያንም ልጅ [[ዩፒተር ኦሊምፑስ]]ን ማርኮ እርሱን የግብጽ አገረ ገዥ አደረገው።