ከ«ካም» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 24፦
በኋላ አሕዛብ ወደ ርስቶቻቸው ተበትነው ካም ወደ አፍሪካ ሔዶ፣ ከጊዜ በኋላ በ[[ግብጽ]] ላይ ወረደ፣ በዚያ አስማት በማስተማሩ የሰው ልጆች መልካም ጸባይ አወከ። አሕዛብ ከተበተኑ 112 አመታት በኋላ ካሜሴኑስ ከብዙ ሕዝብ ጋራ ከአፍሪካ በ[[ጣልያን]] ላይ ደረሰ፤ እዚያም መንግስቱን ይዞ ወንጄል አሰተማረ። ከ25 አመት በኋላ ግን [[ያኑስ]] በጣልያ ደርሶ ካሜሴኑስ ጥፋት በማስተምር አግኝቶት ይህንን ሁኔታ ለ3 ዓመት ከታገሠ በኋላ ያኑስ ካሜሴኑስን ከጣልያን አባረረው። ካሜሴኑስም ወደ [[ሲሲሊያ]]<ref>በሲሲሊያ ደሴት አሁን [[አቺሬያሌ]] በተባለው ከተማ ልማድ፣ ከተማው «ካሜሴና» ተብሎ በካሜሴኑስ (ካም) እራሱ እንደ ተመሠረተ የሚል ጥንታዊ ጽሑፍ ተቀርጾ ይገኛል። Brydone's Tour through Sicily & Malta, 1840, p. 73-74.</ref> እንደ ሸሸ ይጻፋል።
 
በዚህ ሰዓት፣ የካም እኅት የኖህም ሴት ልጅ [[ሬያ]] የ[[ሊብያ]] ንጉሥ [[ሃሞን]] ንግስት ስትሆን ሃሞን ግን ከሌላይቱ ሴት ከ[[አልማንጤያ]] ጋር ልጁን [[ዲዮኒስዮስ]]ን ወልዶ ሬያም በቅናት ተቆጥታ፣ ልጁን በ[[ኒሳ (አፈ ታሪክ)|ኒሳ]] ከተማ በሥውር እንዲያድግ ተላከ። (ይህም ታሪክ ከጥንታዊ ግሪክ ትውፊቶች ጋር ተመሳሳይነት አለው።) ሆኖም ሬያ በቅናቷ ተይዛ ከሃሞን ለቅቃ ወጥታ ወደ ወንድሟ ወደ ካሜሴኑስ በሲኪሊያ ሄደች። ካሜሴኑስ ሕጋዊ ሚስቱን ኖኤላን (በመርከብ ያመለጠችው የአፍሪካውያን ዘር እናት) ከዚህ በፊት ትቶ ነበር፤ አሁንም ካምና እህቱ ሬያ በሲኪሊያ ብዙም ታላላቅ አይነት ሰዎች ዘር ወለዱ። ካሜሴኑስና ሬያ ከ16 '[[ቲታኖች]]' ጋር ከዚያ የሃሞንን መንግሥት ሊብያን ወረሩ፤ ሃሞንንም ከሊቢያ ወደ [[ክሬታ]] ደሴት አባረሩት። ያንጊዜ ካሜሴኑስ ወይም ካም ለግዜው የሊቢያ ንጉሥ ሆነ፤ በዚያም ሬያ [[ዩፒተር ኦሲሪስ]]ን ወለደችለት። ነገር ግን የሃሞን ልጅ ዲዮኒስዮስ አድጎ ከኒሳ ደርሶ የአባቱንም ቂም በቅሎ ካምንና ሬያን ከሊቢያ አባረራቸው። ዲዮኒስዮስም ልጃቸውን ኦሲሪስን ማርኮት እንጀራ-አባቱ ሆነና እሱን የግብጽ ፈርዖን እንዲሆን አደረገው።
 
ካምና ሬያ ግን ከሊቢያ ወደ ግብጽ በስደት ተመለሡ። በዚያ (አሕዛብ ከተበተኑት 171 ዓመታት በኋላ) አንዲትን ሴት ልጅ «ዩኖ አይጊፕቲያ» ወይም [[ኢሲስ]]ን ወለዱ። ካሜሴኑስ ግን ከግብጽ ወደ [[ባክትሪያ]] (በ[[ፋርስ]]) ሄደ፣ በዚያም ሕዝቡን በተንኮል መራቸው። አሕዛብ የተበተኑት 250 አመት ሳይደርስ፣ ካሜሴኑስ ከባክትሪያ ገስሶ በ[[አሦር]] ንጉሥ [[ኒኑስ]] ላይ ጦርነት አድርጎ በዚያ ዘመቻ ግን ተገደለና ኒኑስ ራሱን አቋረጠው። የኖህ ልጅ ካም መሞት እንዲህ ነበር ዮሐንስ ዴ ቪቴርቦ ጥንታዊ ነው ብሎ ያሳተመው ዜና መዋዕል እንደሚነግረን። ይህም በ[[16ኛው ክፍለ ዘመን]] ዓ.ም. በሰፊው የሚታመን ከሆነ፣ በኋላ ግን የአውሮጳ መምህሮች ጽሁፉ በሙሉ ሓሣዊ መሆን አለበት ብለው ገመቱ።
ከ «https://am.wikipedia.org/wiki/ካም» የተወሰደ