ከ«ክሮኖስ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
No edit summary
መስመር፡ 7፦
ከዚሁ በኋላ ክሮኖስ ዕኅቱን [[ሬያ]]ን አገባትና ንጉሥና ንግሥት ሆነው ዓለሙን ገዙ። ይህም «ወርቃማ ዘመን» የተባለው ነበር፤ እያንዳንዱ ግለሠብ በምግባር ስለ ሠራ ለድንጋጌዎች አስፈላጊነት ያልነበረበት ወቅት መሆኑ ታመነ።
 
ክሮኖስና ሬያ ብዙ ሌሎች አማላክት ወለዱ፦ [[ዴሜቴር]]፣ [[ሄራ]]፣ ሃይዴስ፣ [[ሄስቲያ]] እና ፖሠይዶን ነበሩ። ዳሩ ግን ክሮኖስ በገዛው ልጆች እንዲገለበጥ ስለሚል ትንቢት፣ እያንዳንዱ እንደ ተወለደ እርሱ በላቸው። ስለዚህ ስድስተኛው ልጅ ዚውስ ሲወለድ እናቱ በስውር ቦታ በ[[ክሬታ]] ደሴት እንዲታደግ አደረገች። ከታደገ በኋላ ዚውስ መድኃኒት ለክሮኖስ አጠጣውና ወንድሞቹን እንዲያውካቸው አስደረገው። ዚውስ፣ ወንድሞቹና ጊጋንቴስ ከክሮኖስ ኃያላት ጋር [[ቲታኖማኬ]] የተባለ አፈታሪካዊ ጦርነት ተዋጉ። ከዚሁ ጦርነት በኋላ ክሮኖስ በታርታሮስ ታሠረ። በ[[ፒንዳር]] ዕትም ግን ክሮኖስ ከዚያ በኋላ ወጣና የ[[ኤሊሲዩም]] ንጉሥ ሆነ። [[ዊርጊል]] ደግሞ እንደጻፈው፣ ሳቱርን (ክሮኖስ) ከዚያ ወጥቶ የ[[ላቲዩም]] (በ[[ጣልያን]]) ንጉስ ሆነ።
 
በጣልያን አፈ ታሪክ ረገድ ደግሞ የክሮኖስ ወይም የስቱርን ስም አንዳንዴ ከ«ካሜሲስ» ወይም ከ«ካሜሴኑስ» ስም ጋር ይለዋወጣል። ለምሳሌ [[አኒዩስ ዳ ቪቴርቦ]] ባሳተመው ዜና መዋዕል ውስጥ፣ «ሳቱርን» እንደ ማዕረግ ሲቆጠር፣ መጀመርያውም «የ[[ባቢሎን]] ሳቱርን» [[ናምሩድ]] ሲባል፣ ካዚያ የ[[ኖኅ]] ልጅ [[ካም]] (ወይም ካሜሴኑስ) «የግብጻውያን ሳቱርን» ከዚያ በ[[ሊብያ]]፣ በጣልያንና በ[[ባክትሪያ]] በተራ ይገዛል፤ ከ[[ሃሞን]]፣ ከቲታኖችና በኋላም ከ[[ኒንያስ]] ጋር ይዋጋል።