ከ«ክሮኖስ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
r2.7.1) (ሎሌ መጨመር: af, ar, ast, az, be, bg, bn, br, bs, ca, cs, cy, da, de, el, eo, es, et, eu, fa, fi, fr, gl, he, hi, hr, hsb, id, is, it, ja, jv, ka, ko, la, lb, lt, lv, mk, mn, nl, nn, no, pl, pt, ru, sh, simple, sk, sl, sr, sv, th, tl
No edit summary
መስመር፡ 9፦
ክሮኖስና ሬያ ብዙ ሌሎች አማላክት ወለዱ፦ [[ዴሜቴር]]፣ [[ሄራ]]፣ ሃይዴስ፣ [[ሄስቲያ]] እና ፖሠይዶን ነበሩ። ዳሩ ግን ክሮኖስ በገዛው ልጆች እንዲገለበጥ ስለሚል ትንቢት፣ እያንዳንዱ እንደ ተወለደ እርሱ በላቸው። ስለዚህ ስድስተኛው ልጅ ዚውስ ሲወለድ በስውር ቦታ በ[[ክሬታ]] ደሴት እንዲታደግ አደረገች። ከታደገ በኋላ ዚውስ መድኃኒት ለክሮኖስ አጠጣውና ወንድሞቹን እንዲያውካቸው አስደረገው። ዚውስ፣ ወንድሞቹና ጊጋንቴስ ከክሮኖስ ኃያላት ጋር [[ቲታኖማኬ]] የተባለ አፈታሪካዊ ጦርነት ተዋጉ። ከዚሁ ጦርነት በኋላ ክሮኖስ በታርታሮስ ታሠረ። በ[[ፒንዳር]] ዕትም ግን ከዚያ በኋላ ወጣና የ[[ኤሊሲዩም]] ንጉሥ ሆነ። [[ዊርጊል]] ደግሞ እንደጻፈው፣ ሳቱርን (ክሮኖስ) ከዚያ ወጥቶ የ[[ላቲዩም]] (በ[[ጣልያን]]) ንጉስ ሆነ።
 
በጣልያን አፈ ታሪክ ረገድ ደግሞ የክሮኖስ ወይም የስቱርን ስም አንዳንዴ ከ«ካሜሲስ» ወይም ከ«ካሜሴኑስ» ስም ጋር ይለዋወጣል። ለምሳሌ [[አኒዩስ ዳ ቪቴርቦ]] ባሳተመው ዜና መዋዕል ውስጥ፣ «ሳቱርን» እንደ ማዕረግ ሲቆጠር፣ መጀመርያውም «የ[[ባቢሎን]] ሳቱርን» [[ናምሩድ]] ሲባል፣ ካዚያ የ[[ኖኅ]] ልጅ [[ካም]] (ወይም ካሜሴኑስ) «የግብጻውያን ሳቱርን» ከዚያ በ[[ሊብያ]]፣ በጣልያንና በ[[ባክትሪያ]] በተራ ይገዛል፤ ከ[[ሃሞን]]፣ ከቲታኖችና በኋላም ከ[[ኒንያስ]] ጋር ይዋጋል።
==በዲዮዶሩስ ሲኩሉስ==
[[ዲዮዶሮስ ሲኩሉስ]] በመዘገበው የ[[ሊብያ]] አፈ ታሪክ ዘንድ፣ ክሮኖስ ወይም ሳቱርን የኡራኖስና የ[[ቲቴያ]] ልጅ ሲሆን በጣልያን፣ [[ሲኪልያ]]ና [[ስሜን አፍሪካ]] ላይ ንጉሥ ነበረ። ለዚህ እንደ ማስረጃ በሲኪሊያ የተገኙ ''ክሮኒያ'' የተባሉትን ኮረብታዎች ይጠቅሳል። ክሮኖስና ቲታኖች በወንድሙ በክሬታ ንጉሥ በ[[ዩፒተር]] (ዚውስ) እና በ[[ኒሳ]] ንጉሥ በ[[ሃሞን]] ላይ ጦርነት ያደርጋል፤ ኒሳ በ[[አፍሪካ]] ውስጥ በ[[ትሪቶኒስ ሀይቅ|ትሪቶን ወንዝ]] የሚገኝ ደሴት ነው። ክሮኖስ ድል አድርጎ እኅቱን ሬያን ሚስቱ እንድትሆን ከሃሞን ይሠርቃታል። ነገር ግን የሃሞን ልጅ [[ዲዮኒስዮስ]] ([[ባኩስ]]) በፋንታው ክሮኖስን ድል ያደርጋል፤ ከዚያ የክሮኖስና የሬያ ልጅ [[ዩፒተር ኦሊምፑስ]] የ[[ግብፅ]] አገረ ገዥ እንዲሆን ባኩስ ያሾመዋል። ባኩስና ዩፖተር ኦሊምፑስ ከዚያ የቀሩትን ቲታኖች በክሬታ ደሴት ያሸንፋቸዋል። ባኩስ ከሞተ በኋላ ዩፕተር ኦሊምፑስ መንግሥታትን ሁሉ ወርሶ የአለም ጌታ ሆነ። (ዲዮዶሩስ መጽሐፍ 3)