ከ«ክሮኖስ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 12፦
[[ዲዮዶሮስ ሲኩሉስ]] በመዘገበው የ[[ሊብያ]] አፈ ታሪክ ዘንድ፣ ክሮኖስ ወይም ሳቱርን የኡራኖስና የ[[ቲቴያ]] ልጅ ሲሆን በጣልያን፣ [[ሲኪልያ]]ና [[ስሜን አፍሪካ]] ላይ ንጉሥ ነበረ። ለዚህ እንደ ማስረጃ በሲኪሊያ የተገኙ ''ክሮኒያ'' የተባሉትን ኮረብታዎች ይጠቅሳል። ክሮኖስና ቲታኖች በወንድሙ በክሬታ ንጉሥ በ[[ዩፒተር]] (ዚውስ) እና በ[[ኒሳ]] ንጉሥ በ[[ሃሞን]] ላይ ጦርነት ያደርጋል፤ ኒሳ በ[[አፍሪካ]] ውስጥ በ[[ትሪቶኒስ ሀይቅ|ትሪቶን ወንዝ]] የሚገኝ ደሴት ነው። ክሮኖስ ድል አድርጎ እኅቱን ሬያን ሚስቱ እንድትሆን ከሃሞን ይሠርቃታል። ነገር ግን የሃሞን ልጅ [[ዲዮኒስዮስ]] ([[ባኩስ]]) በፋንታው ክሮኖስን ድል ያደርጋል፤ ከዚያ የክሮኖስና የሬያ ልጅ [[ዩፒተር ኦሊምፑስ]] የ[[ግብፅ]] አገረ ገዥ እንዲሆን ባኩስ ያሾመዋል። ባኩስና ዩፖተር ኦሊምፑስ ከዚያ የቀሩትን ቲታኖች በክሬታ ደሴት ያሸንፋቸዋል። ባኩስ ከሞተ በኋላ ዩፕተር ኦሊምፑስ መንግሥታትን ሁሉ ወርሶ የአለም ጌታ ሆነ። (ዲዮዶሩስ መጽሐፍ 3)
 
==በሲቢሊን ራዕዮች==
[[የሲቢሊን ራዕዮች]] እንደገና ክሮኖስን ይጠቅሳል፤ በተለይ በ3ኛው መጽሐፍ ዘንድ የኡራኖስና ጋያ 3 ልጆች ክሮኖስ፣ ቲታንና [[ያፔቱስ]] ይባላሉ። እያንዳንዱ ወንድም የመሬቱን ሢሶ በርስት ይቀበላል፤ ክሮኖስም በሁላቸው ላይ ንጉሥ ይደረጋል። ኡራኖስ ከሞተ በኋላ፣ የቲታን ልጆች የክሮኖስና የሬያ ልጆች እንደተወለዱ ሊያጥፏቸው ይሞክራሉ። ነገር ግን ሬያ በ[[ዶዶና]] ልጆቿን ዚውስን፣ ፖሠይዶንንና ሃይዴስን በሥውር ወለደች፤ በ3 ክሬታዊ ሰዎች ጥብቅና እንዲታድጉ ወደ [[ፍርግያ]] ትልካቸዋለች። ይህንን ባወቁ ጊዜ፣ ከቲታን ወገን 60 ሰዎች ክሮኖስንና ሬያን ይሥራሉ፤ ስለዚህ የክሮኖስ ልጆች መጀመርያውን ጦርነት በቲታን ወገን ላይ ይሠራሉ። በዚሁ ታሪክ ክሮኖስ አባቱን ወይም ልጆቹን ስለ መግደሉ ምንም ቃል የለም።