ከ«ሙሴ ቀስተኛ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
Robot-assisted disambiguation: ግሪክ - Changed link(s) to ግሪክ (አገር)
No edit summary
መስመር፡ 1፦
'''ሙሴ ቀስተኛ ((ሴባስቲያኖ ካስታኛ)ጣልያንኛ፡ Sebastiano Castagna)''' ይሄ ሰው በ[[አድዋ ጦርነት]] የ[[ጣልያን]] መንግሥት አገራችንን [[ኢትዮጵያ]]ን በቅኝ ግዛትነት ለመግዛት ከገቡት ወታደሮች አንዱ ሲሆን፣ ለወረራ የመጣው የጠላት ኃይል በ[[ዳግማዊ ምኒልክ|ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ]] እና በሠራዊታቸው ቆራጥነት አድዋ ላይ ድል ሲሆን ተማርኮ የቀረና እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ ኢትዮጵያ ውስጥ የኖር ኢጣልያዊ ነው።
 
ሙሴ ቀስተኛ በ[[1860|፲፰፻፷]] ዓ/ም በ[[ሲሲሊ]] ደሴት አይዶኔ በሚባል ሥፍራ ተወለደ። ስለልጅነት ዘመኖቹ እና በወጣትነቱም የ[[ጣልያን]]ን የጦር ሠራዊት እንዴት እና ለምን እንደተቆራኘ መቼ፣ ከማን ሠራዊት ጋር፣ የትኛው ወደብ ላይ ኢትዮጵያ ላይ ለመዝመት እንደመጣ በእርግጠኛነት ባይታወቅም፤ ድሉ የ[[ኢትዮጵያ]] ሆኖ ሙሴ ቀስተኛ በምርኮኛነት በ[[ዳግማዊ ምኒልክ|ዳግማዊ ዓፄ ምኒልክ]] ሠራዊት እጅ ወደቀ። ከተማረከም በኋላ በፈቃዳቸው እዚያው ኢትዮጵያ ውስጥ ከቀሩት ብዙ ጣልያኖች አንዱ እንደነበረና በተግባረ ዕድ ሞያው ታዋቂነትን አትርፎ በምህንድስና ተግባራት እንደተሰማራና ኢትዮጵያም ውስጥ እስከ ሁለተኛው የ[[ፋሽስት ኢጣልያ]] ወረራ ድረስ ኖሯል። በወረራውም ጊዜ የጣልያንን ጦር ዓለቆች በሰላይነት እንዳገለገላቸውና በመጨረሻም በአንድ ቆራጥ ኢትዮጵያዊ [[አርበኛ]] እጅ ሕይወቱን እንዳጣ ስለእሱ ከተጻፉ ጥቂት ታሪካዊ መሥመሮች ላይ እንገነዘባለን።