ከ«ካም» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 20፦
==«ሐሣዊ ቤሮሶስ» በተባለው ዜና መዋዕል==
 
በ[[1490]] ዓ.ም. በጣልያናዊ መነኩሴ [[አኒዩስ ዴ ቪቴርቦ]] የታተመው «ሐሣዊ ቤሮሶስ» የተባለው ዜና መዋዕል ስለ ካም ሕይወት ብዙ ተጨማሪ መረጃ አለው። በዚህ በኩል፣ የኖህ ቤተሠብ ከመርከብ ወጥተው በ[[አርሜኒያ]] ገና ሲኖሩ፣ ካም ከጥፋት ውኃ በፊት የነበረውን ክፉ አስማት ተማረ፤ ደግሞ እሱ መጀመርያው [[ዞራስተር]] የተባለው ሆነ። ሌላ ስሙ «ካም ኤሴኑስ» (ካም መረኑ) እና [[ሳቱርን]] ([[ክሮኖስ]]) እንደ ነበር ይላል። ኖህ ከጥፋት ውሃ በኋላ ሌሎችን ሕጻናት ስለ ወለደ፣ ካም ኤሴኑስ በተለይ ቀናተኛ ሆነና አባቱን ጠላው። አንድ ቀን አባቱ ኖህ በድንኳኑ ሲሰከር በእራቁቱም ሲተኛ ካም አይቶ የሟርት ዘፈን በመዘምሩ በዚህ ምታት ጠንቅ ለጥቂት ዘመንጊዜያዊ የወንድ አለመቻል በኖህ ላይ ደረሰበት።ደረሰበት፤ ኖህም ከዚያ ለጥቂት ወራት ልጅን መውለድ አልቻለም ነበር።
 
በኋላ አሕዛብ ወደ ርስቶቻቸው ተበትነው ካም ወደ አፍሪካ ሔዶ፣ ከጊዜ በኋላ በ[[ግብጽ]] ላይ ወረደ፣ በዚያ አስማት በማስተማሩ የሰው ልጆች መልካም ጸባይ አወከ። አሕዛብ ከተበተኑ 112 አመታት በኋላ ካሜሴኑስ ከብዙ ሕዝብ ጋራ ከአፍሪካ በ[[ጣልያን]] ላይ ደረሰ፤ እዚያም መንግስቱን ይዞ ወንጄል አሰተማረ። ከ25 አመት በኋላ ግን [[ያኑስ]] በጣልያ ደርሶ ካሜሴኑስ ጥፋት በማስተምር አግኝቶት ይህንን ሁኔታ ለ3 ዓመት ከታገሠ በኋላ ያኑስ ካሜሴኑስን ከጣልያን አባረረው። ካሜሴኑስም ወደ [[ሲሲሊያ]]<ref>በሲሲሊያ ደሴት አሁን [[አቺሬያሌ]] በተባለው ከተማ ልማድ፣ ከተማው «ካሜሴና» ተብሎ በካሜሴኑስ (ካም) እራሱ እንደ ተመሠረተ የሚል ጥንታዊ ጽሑፍ ተቀርጾ ይገኛል። Brydone's Tour through Sicily & Malta, 1840, p. 73-74.</ref> እንደ ሸሸ ይጻፋል።
ከ «https://am.wikipedia.org/wiki/ካም» የተወሰደ