ከ«ካም» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 2፦
 
==ልደት==
ካም የተወለደው ከ[[ማየ አይኅ]] አስቀድሞ እንደ ነበር ይታመናል። ኦሪት ዘፍጥረት 5፡32 እንደሚለን፣ «ኖኅም የአምስት መቶ አመት ሰው ነበረ፤ ኖኅም [[ሴም]]ን ካምን [[ያፌት]]ንም ወለደ።» በ[[መጽሐፈ ኩፋሌ]] አቆጣጠር፣ ኖህ በ[[ዓመተ ዓለም]] 707 ተወልዶ፣ ሴምን በ1207 ዓ.ዓ. ሴምን ወለደ፤ በ1209 ዓ.ዓ. ካምንም፣ በ1212 ዓ.ዓ. ያፌትንም ወለዳቸው። በዚህ አቆጣጠር በ1308 ዓ.ዓ. ማየ አይኅ ወይም የጥፋት ውኃ በደረሰበት ዓመት የካም ዕድሜ 99 ዓመት ያህል ነበር። በዚያ ዘመን የአበው ዕድሜ እስከ ሺ ድረስ ሊሆን ስለሚችል ይህ እንደ ወጣት መቆጠሩ ማለት ነው።
 
የሚስቱ ስም በዘፍጥረት ባይጻፍም በኩፋሌ ግን ስሟ ናኤልታማኡክ (ወይም ኔኤላታማኡክ፣ አኤልታማኡክ) እንደ ነበር ይተረካል። በ[[ሚስቶች በኖህ መርከብ ላይ|ሌላ ጥንታዊ ምንጮች ዘንድ]] ስሟ ናሐላጥ፣ ኖኤላ፣ ናሕላብ፣ ወዘተ. የሚመስል ነበር። እነዚህ ሁለቱ ከውኃው በ[[የኖህ መርከብ|ኖህ መርከብ]] ያመለጠው የ8 ሰዎች ቤተሠብ መካከል ነበሩ።
ከ «https://am.wikipedia.org/wiki/ካም» የተወሰደ