ከ«ካም» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 12፦
በኩፋሌ ዘንድ በ1569 ዓ.ዓ. ምድር በኖህ 3 ልጆች መካከል በ3 ክፍሎች ተካፈለች። እንዲሁም በነዚህ 3 ዋና ክፍሎች ውስጥ ለኖህ 16 ልጅ-ልጆች 16 ርስቶች ተሰጡ። ለካምና ለልጆቹ የደረሰው ክፍል ከ[[ግዮን ወንዝ]] ወደ ምዕራብ ያለው ሁሉ፣ ከዚያም ከ[[ገዲር]] ደቡብ ያለው ሁሉ ሆነ። ይህም የምድር አከፋፈል በብዙ ሌሎች ጥንታዊ ምንጮች ይጠቀሳል። ማንም የወንድሙን ርስት በግድ እንዳይዝ የሚል ተጨማሪ ርጉም እንዲኖር ተዋዋሉ።
 
በ1596 እስከ 1639 ዓ.ዓ. ድረስ፣ የሰው ልጆች በዝተው በ[[ሰነዓርሰናዖር]] ሰፍረው [[የባቢሎን ግንብ]] ሠሩ። በዚህ ላይ ንጉሣቸው የካም ልጅ ኩሽ ልጅ [[ናምሩድ]] እንደ ነበር በብዙ ምንጭ ይባላል። ከ1639 ዓ.ዓ. ጀምሮ የኖህ ልጆች ወገኖቻቸውን ወደየርስቶቻቸው ይወስዱ እንደ ጀመር ደግሞ በመጽሐፈ ኩፋሌ አለ። በዚህ ሰዓት ካም፣ 4 ልጆቹና ቤተሠቦቻቸው ሁሉ ከሰነዓር ወደ [[አፍሪቃ]] ወደ ድርሻቸው ይጓዙ ጀመር። ዳሩ ግን በ[[ሊባኖስ]] ዙሪያ ሲደርሱ ከነዓን በዚያ ቁጭ ብሎ እሱ መጀመርያ መሓላቸውን ሰበረ። ያው አገር በሴም ልጅ [[አርፋክስድ]] ርስት ስለ ነበር ነው። አባቱ ካምና 3 ወንድሞቹ መንገዱን እንዲከተል ቢለምኑትም ከነዓን እምቢ እንዳላቸው በኩፋሌ ይነባል። ካም ግን ከ3ቱ ልጆቹ ጋር እስከ አፍሪካና እስከ ግዮን ወንዝ ድረስ መንገዳቸውን ተከተሉ።
 
==የኢትዮጵያ ልማድ==
ከ «https://am.wikipedia.org/wiki/ካም» የተወሰደ