ከ«ካም» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 28፦
ካምና ሬያ ግን ከሊቢያ ወደ ግብጽ በስደት ተመለሡ። በዚያ (አሕዛብ ከተበተኑት 171 ዓመታት በኋላ) አንዲትን ሴት ልጅ «ዩኖ አይጊፕቲያ» ወይም [[ኢሲስ]]ን ወለዱ። ካሜሴኑስ ግን ከግብጽ ወደ [[ባክቲርያ]] (በ[[ፋርስ]]) ሄደ፣ በዚያም ሕዝቡን በተንኮል መራቸው። አሕዛብ የተበተኑት 250 አመት ሳይደርስ፣ ካሜሴኑስ ከባክትሪያ ገስሶ በ[[አሦር]] ንጉሥ [[ኒኑስ]] ላይ ጦርነት አድርጎ በዚያ ዘመቻ ግን ተገደለና ኒኑስ ራሱን አቋረጠው። የኖህ ልጅ ካም መሞት እንዲህ ነበር ዮሐንስ ዴ ቪቴርቦ ጥንታዊ ነው ብሎ ያሳተመው ዜና መዋዕል እንደሚነግረን። ይህም በ[[16ኛው ክፍለ ዘመን]] ዓ.ም. በሰፊው የሚታመን ከሆነ፣ በኋላ ግን የአውሮጳ መምህሮች ጽሁፉ በሙሉ ሓሣዊ መሆን አለበት ብለው ገመቱ።
 
==አል-ታባሪ==
 
የፋርስ ታሪክ ጸሐፊ [[ሙሐማድ ኢብን ጃሪር አል-ታባሪ]] በ907 ዓ.ም. ግድም በጻፈው ''[[የነቢያትና የነገሥታት ታሪክ]]'' ስለ ካም ተጨማሪ ትውፊት አለው። ይህ በጣም ግሩም ትውፊት ግን ስለ ካም ሕይወት ዘመን ነው ሊባል አይችልም። በዚህ አፈ ታሪክ ዘንድ፣ አንድ ቀን የ[[ኢየሱስ]] [[ሐዋርያት]] ስለ ኖህ (ኑኅ) መርከብ ምስጢራዊ መረጃ ለማወቅ ኢየሱስን ለመኑት። ኢየሱስም መልሶ ለጥቂት ጊዜ የኖህን ልጅ ካም ከሞት አነሣው። ያንጊዜ ካም እራሱ ስለ መርከቡ አንድ ትምህርት ይሰጣቸዋል። ካም በሰጣቸውም መረጃ ዘንድ፣ በመርከቡ ላይ ቆሻሻ በበዛበት ጊዜ፣ ኑህ በተዓምር [[ዐሣማ]]ዎች ከ[[ዝሆን]] [[ኩምቢ]] አወጣ፤ እንደገና [[አይጥ]] ያለ ፈቃድ በመርከቡ ስለ ገባ [[ድመት]] ከ[[አንበሣ]] አፍንጫ ፈጠረ አላቸው። እነዚህ ተአምራት በ[[ቁርዓን]] ስለማይገኙ ግን ብዙዎቹ እስላሞች አይቀብሉዋቸውም።<ref>[http://books.google.com/books?id=gTPB-PCAMGwC&lpg=PA357&dq=%22would%20that%20you%20send%20us%20a%20man%20who%20saw%20the%20ark%22&pg=PA357#v=onepage&q=%22would%20that%20you%20send%20us%20a%20man%20who%20saw%20the%20ark%22&f=false አል-ታባሪ፣ የነቢያትና የነገሥታት ታሪክ] {{en}}<ref>
 
 
{{መዋቅር-ሃይማኖት}}
 
{{የኖህ ልጆች}}
ከ «https://am.wikipedia.org/wiki/ካም» የተወሰደ