ከ«ካም» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 17፦
 
በአንድ [[ኢትዮጵያ]]ዊ ልማድ ዘንድ፣ ከባቢሎን ግንብ ውድቀት ቀጥሎ ካም የአገሩ መጀምርያው ንጉሥ ነበረ። ለ78 ዓመታት ገዛ፣ ከዚያም በኲሩ ኩሽ በዙፋኑ ተከተለው ይባላል። ይህ መረጃ የሚገኘው በ[[1919]] ዓ.ም. ራስ ተፈሪ (በኋላ አጼ [[ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ]]) ለጸሐፊው [[ቻርልስ ረይ]] ካቀረቡት ልማዳዊ [[የኢትዮጵያ ነገሥታት]] ዝርዝር ላይ ነው። ከዚህ ዘመን በኋላ ካም [[ሶርያ]]ን በወረረበት ጊዜ እንደ ተገደለ በአንዳንድ የሀገር ታሪክ ጸሐፍት ይጨመራል።
 
==«ሐሣዊ ቤሮሶስ» በተባለው ዜና መዋዕል==
 
በ[[1490]] ዓ.ም. በጣልያናዊ መነኩሴ [[አኒዩስ ዴ ቪቴርቦ]] የታተመው «ሐሣዊ ቤሮሶስ» የተባለው ዜና መዋዕል ስለ ካም ሕይወት ብዙ ተጨማሪ መረጀ አለው። በዚህ በኩል፣ ከመርከብ ወጥተው በ[[አርሜኒያ]] ገና ሲኖሩ፣ ካም ከጥፋት ውኃ በፊት የነበረውን ክፉ አስማት ተማረ፤ ደግሞ እሱ መጀመርያው [[ዞራስተር]] የተባለው ሆነ። ሌላ ስሙ «ካም ኤሴኑስ» (ካም መረኑ) እንደ ነበር ይላል። ኖህ ከጥፋት ውሃ በኋላ ሌሎችን ሕጻናት ስለ ወለደ፣ ካም በተለይ ቀናተኛ ሆነና አባቱን ጠላው። አንድ ቀን አባቱ ኖህ በድንኳኑ ሲሰከር በእራቁቱም ሲተኛ አይቶ ካም የሟርት ዘፈን በመዘምሩ በዚህ ምታት ጠንቅ ለጥቂት ዘመን የወንድ አለመቻል በኖህ ላይ ደረሰበት።
 
በኋላ አሕዛብ ወደ ርስቶቻቸው ተበትነው ካም ወደ አፍሪካ ሔዶ፣ ከጊዜ በኋላ በ[[ግብጽ]] ላይ ወረደ፣ በዚያ አስማት በማስተማሩ የሰው ልጆች መልካም ጸባይ አወከ። አሕዛብ ከተበተኑ 112 አመታት በኋላ ካም ከብዙ ሕዝብ ጋራ ከአፍሪካ በ[[ጣልያን]] ላይ ደረሰ፤ እዚያም መንግስቱን ይዞ ወንጄል አሰተማረ። ከ25 አመት በኋላ [[ያኑስ]] በጣልያ ደርሶ
 
{{መዋቅር-ሃይማኖት}}
ከ «https://am.wikipedia.org/wiki/ካም» የተወሰደ