ከ«ካም» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 7፦
 
==የከነዓን መረገም==
በዘፍጥረት 9፡20-27 አንድ ታሪክ ስለ ካም አለ። ትንሽ ከጥፋት ውኃ በኋላ ቤተሠቡ ገና በ[[አራራት]] ተራራ ሲኖሩ አባቱ ኖህ ሰክሮ ካም በዕራቁትነቱ እንዳየው ይላል። ስለዚህ ኖኅ ተቆጥቶ በካም ታናሽ ልጅ ከነዓን ላይ ርጉም ጣለ። በኩፋሌ ዘንድ ይህ የሆነበት በ1321 ዓ.ዓ. ወይም መርከቡ ከቆመው 12 ዓመታት በኋላ ነበር። ካም ከዚያ ወጥቶ ከተማ በአራራት ደቡብ ገጽ በሚስቱ ስም እንደ ሠራ በኩፋሌ ይጨመራል። ከዚያ ሴምና ያፌት በሚስቶቻቸውም ስሞች ለራሳቸው ከተሞች በዙሪያው ሠሩ ይላል።
 
==የምድር አከፋፈል==
በኩፋሌ ዘንድ በ1569 ዓ.ዓ. ምድር በኖህ 3 ልጆች መካከል በ3 ክፍሎች ተካፈለች። እንዲሁም በነዚህ 3 ዋና ክፍሎች ውስጥ ለኖህ 16 ልጅ-ልጆች 16 ርስቶች ተሰጡ። ለካምና ለልጆቹ የደረሰው ክፍል ከ[[ግዮን ወንዝ]] ወደ ምዕራብ ያለው ሁሉ፣ ከዚያም ከ[[ገዲር]] ደቡብ ያለው ሁሉ ሆነ። ይህም የምድር አከፋፈል በብዙ ሌሎች ጥንታዊ ምንጮች ይጠቀሳል። ማንም የወንድሙን ርስት በግድ እንዳይዝ የሚል ተጨማሪ ርጉም እንዲኖር ተዋዋሉ።
 
በ1596 እስከ 1639 ዓ.ዓ. ድረስ፣ የሰው ልጆች በዝተው በ[[ሰነዓር]] ሰፍረው [[የባቢሎን ግንብ]] ሠሩ። በዚህ ላይ ንጉሣቸው የካም ልጅ ኩሽ ልጅ [[ናምሩድ]] እንደ ነበር በብዙ ምንጭ ይባላል። ከ1639 ዓ.ዓ. ጀምሮ የኖህ ልጆች ወገኖቻቸውን ወደየርስቶቻቸው ይወስዱ እንደ ጀመር ደግሞ በመጽሐፈ ኩፋሌ አለ። በዚህ ሰዓት ካም፣ 4 ልጆቹና ቤተሠቦቻቸው ሁሉ ከሰነዓር ወደ [[አፍሪቃ]] ወደ ድርሻቸው ይጓዙ ጀመር። ዳሩ ግን በ[[ሊባኖስ]] ዙሪያ ሲደርሱ ከነዓን በዚያ ቁጭ ብሎ እሱ መጀመርያ መሓላቸውን ሰበረ። ያው አገር በሴም ልጅ [[አርፋክስድ]] ርስት ስለ ነበር ነው። አባቱ ካምና 3 ወንድሞቹ መንገዱን እንዲከተል ቢለምኑትም ከነዓን እምቢ እንዳላቸው በኩፋሌ ይነባል። ካም ግን ከ3ቱ ልጆቹ ጋር እስከ አፍሪካና እስከ ግዮን ወንዝ ድረስ መንገዳቸውን ተከተሉ።
 
==የኢትዮጵያ ልማድ==
 
በአንድ [[ኢትዮጵያ]]ዊ ልማድ ዘንድ፣ ከባቢሎን ግንብ ውድቀት ቀጥሎ ካም የአገሩ መጀምርያው ንጉሥ ነበረ። ለ78 ዓመታት ገዛ፣ ከዚያም በኳሩ ኩሽ በዙፋኑ ተከተለው ይባላል። ይህ መረጃ የሚገኘው በ[[1919]] ዓ.ም. ራስ ተፈሪ (በኋላ አጼ [[ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ]]) ለጸሐፊው [[ቻርልስ ረይ]] ካቀረቡት ልማዳዊ [[የኢትዮጵያ ነገሥታት]] ዝርዝር ላይ ነው። ከዚህ ዘመን በኋላ ካም [[ሶርያ]]ን በወረረበት ጊዜ እንደ ተገደለ በአንዳንድ የሀገር ታሪክ ጸሐፍት ይጨመራል።
 
{{መዋቅር-ሃይማኖት}}
ከ «https://am.wikipedia.org/wiki/ካም» የተወሰደ