ከ«ሰብታ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ «'''ሰብታ''' በ''ኦሪት ዘፍጥረት'' ምዕ. 10 መሠረት የኩሽ ሦስተኛ ልጅ ነበር። በአንዳ...»
 
No edit summary
መስመር፡ 3፦
በአንዳንድ ሊቃውንት ዘንድ፣ ሰብታ በ[[አረቢያ]] ዳርቻ (በ[[ቀይ ባህር]] ላይ) ይገኝ የነበረው [[ሳቦታ]] በተባለ ሥፍራ ሰፈረበት። ይህ ሳቦታ የ[[ሃስረሞት]] ዋና ከተማ ነበረች። ሌላ ሊቃውንት እንደሚያስቡት፣ በ[[ሞሮኮ]] ዳርቻ (በ[[ጂብራልታር ወሽመጥ]] ላይ) የሚገኘው [[ሴውታ]] የሰብታ ልጆች መኖራያ ይሆናል። በዚህ ሃሣብ ልጆቹ በሳህራ በረሃ ሠፈሩ።
 
ዳሩ ግን በ[[1ኛው ክፍለ ዘመን]] የጻፈው አይሁዳዊ መምህር [[ፍላቭዩስ ዮሴፉስ]] እንዳለው፣ «የሰብታ ልጆች [[ግሪክ|ግሪኮች]] አሁን አስታቦራውያን የሚሏቸው ናቸው።» በጥንት «አስታቦራስ» ማለት አሁን በ[[ሱዳን]]ና በ[[ኢትዮጵያ]] [[አትባራ ወንዝ]] የሚባል ስለ ሆነ፣ የሰብታ ኩሽ ልጆች በዚያ እንደ ሰፈሩ አመለከተ። በልማዳዊ መዝገብ የተወረሰው [[የኢትዮጵያ ነገሥታት ዝርዝር]] ደግሞ ሰብታ ለ30 አመታት በ[[ኩሽ መንግሥት]] ላይ ንጉሥ ሆነ ይላል፤ ይህም ከ[[ካም]]፣ ኩሽና ሃባሢ በኋላ ሲሆን አመቶቹ ሲቆጠር ምናልባት ከ2259 እስከ 2229 ዓክልበ. ይሆናል። በ[[አኒዩስ]] በተመዘገበ በአንዱ አፈ ታሪክ ዘንድ፣ ይህ ሰብታ ከዚያ ዘመን በፊት በ[[ሳካ]]ዎች ([[እስኩቴስ]]) ላይ የነገሠ ሲሆን፣ ከዚያም ዘመን በኋላ ከአፍሪካ ወደ [[ጣልያን]] ሂዶ በዚያው አገር ደቡብ ክፍል ነገሠ።
 
[[መደብ:የኢትዮጵያ ነገሥታት]]